የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘሌዋውያን 2:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ቍር​ባ​ን​ህም በም​ጣድ የተ​ጋ​ገረ ቍር​ባን ቢሆን፥ በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ የመ​ል​ካም ስንዴ ዱቄት ቂጣ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእህል ቍርባንህ በምጣድ የሚጋገር ከሆነ፣ እርሾ ሳይገባበት በዘይት የተለወሰ የላመ ዱቄት ቂጣ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ቁርባንህም በምጣድ የተጋገረ የእህል ቁርባን ቢሆን፥ እርሾ ያልገባበት፥ በዘይት የተለወሰ የመልካም ዱቄት ቂጣ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

መባው በምጣድ የተጋገረ ኅብስት ከሆነ እርሾ ሳይነካው የወይራ ዘይት ተጨምሮበት ከላመ ዱቄት የተዘጋጀ ይሁን፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ቍርባንህም በምጣድ የተጋገረ የእህል ቍርባን ቢሆን፥ በዘይት የተለወሰ የመልካም ዱቄት ቂጣ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘሌዋውያን 2:5
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቈር​ሰ​ህም ዘይት ታፈ​ስ​ስ​በ​ታ​ለህ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት ነው።


ከዘ​ይት ጋር በም​ጣድ ላይ ያደ​ር​ጉ​ታል፤ ለው​ሰ​ውም ያገ​ቡ​ታል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ፈ​ተት መሥ​ዋ​ዕት ነው።


ለም​ስ​ጋና ቢያ​ቀ​ር​በው፥ ከም​ስ​ጋ​ናው መሥ​ዋ​ዕት ጋር በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ የቂጣ እን​ጎቻ፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ቀባ ስስ ቂጣ፥ በዘ​ይ​ትም የተ​ለ​ወሰ መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት ያቀ​ር​ባል።


በእ​ቶን የተ​ጋ​ገ​ረው የእ​ህል ቍር​ባን ሁሉ፥ በመ​ቀ​ቀ​ያም ወይም በም​ጣድ የበ​ሰ​ለው ሁሉ ለሚ​ያ​ቀ​ር​በው ካህን ይሆ​ናል።


መባ​ውም ለእ​ህል ቍር​ባን በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ መል​ካም ዱቄት የተ​ሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅ​ደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛ​ኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤