የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘሌዋውያን 11:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነገር ግን ከሚ​ያ​መ​ሰ​ኩት ፥ ሰኰ​ና​ቸ​ውም ስን​ጥቅ ከሆ​ነው ከእ​ነ​ዚህ አት​በ​ሉም፤ ግመል ያመ​ሰ​ኳል፤ ነገር ግን ሰኰ​ናው ስላ​ል​ተ​ሰ​ነ​ጠቀ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘የሚያመሰኩ ሆነው ሰኰናቸው ያልተሰነጠቀ ወይም ሰኰናቸው የተሰነጠቀ ሆኖ የማያመሰኩትን አትብሉ፤ ግመል ያመሰኳል፤ ሰኰናው ስላልተሰነጠቀ ግን በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን ከሚያመሰኩት፥ ሰኮናቸውም ስንጥቅ ከሆነው ከእነዚህ አትበሉም፤ ግመል ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኮናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን ከሚያመሰኩት ወይም ሰኮናቸው ስንጥቅ ከሆነው የሚከተሉትን አትበሉም፤ ግመል ያመሰኳል፤ ነገር ግን ሰኰናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን ከሚያመሰኩት፥ ሰኮናቸውም ስንጥቅ ከሆነው ከእነዚህ አትበሉም፤ ግመል ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኮናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘሌዋውያን 11:4
4 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩ​አ​ቸው፦ በም​ድር ካሉት እን​ስ​ሳት ሁሉ የም​ት​በ​ሉ​አ​ቸው እን​ስ​ሳት እነ​ዚህ ናቸው።


የተ​ሰ​ነ​ጠቀ ሰኰና ያለ​ው​ንና የሚ​ያ​መ​ሰ​ኳ​ውን እን​ስሳ ሁሉ ብሉ።


ጥን​ቸል ያመ​ሰ​ኳል፤ ነገር ግን ሰኰ​ናው ስላ​ል​ተ​ሰ​ነ​ጠቀ ይህ ለእ​ና​ንተ ርኩስ ነው።


ጴጥ​ሮስ ግን፥ “አቤቱ፥ ከቶ አይ​ሆ​ንም፤ ርኩስ፥ የሚ​ያ​ጸ​ይ​ፍም ከቶ በልች አላ​ው​ቅም” አለው።