የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘሌዋውያን 1:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ ሙሴን ጠርቶ እን​ዲህ ሲል ተና​ገ​ረው፦

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው፤ ከመገናኛውም ድንኳን እንዲህ ሲል ተናገረው፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም ሙሴን ጠርቶ ከመገናኛው ድንኳን እንዲህ ሲል ተናገረው፦

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሆኖ እግዚአብሔር ሙሴን ጠራው፤ እንዲህ ብሎም አዘዘው፥

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም ከመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሙሴን ጠርቶ እንዲህ ሲል ተናገረው፦

ምዕራፉን ተመልከት



ዘሌዋውያን 1:1
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉ​ንም ቍር​ባን አሳ​ረገ፤ የመ​ጠ​ጡ​ንም ቍር​ባን አፈ​ሰሰ፤ የደ​ኅ​ን​ነ​ቱ​ንም መሥ​ዋ​ዕት ደም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ረጨ።


ጉባ​ኤ​ውም ያመ​ጡት የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ቍጥር ሰባ ወይ​ፈን፥ መቶም አውራ በጎች፥ ሁለት መቶም የበግ ጠቦ​ቶች ነበረ፤ ይህ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነበረ።


ሙሴም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከተ​ራ​ራው ጠርቶ አለው፥ “ለያ​ዕ​ቆብ ቤት እን​ዲህ በል፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ንገር፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “ወደ እኔ ወደ ተራ​ራው ውጣ፤ በዚ​ያም ሁን፤ እኔ የጻ​ፍ​ሁ​ትን ሕግና ትእ​ዛዝ፥ የድ​ን​ጋ​ይም ጽላት እሰ​ጥ​ሃ​ለሁ፤ ሕግ​ንም ትሠ​ራ​ላ​ቸ​ዋ​ለህ” አለው።


በዚ​ያም እገ​ለ​ጥ​ል​ሃ​ለሁ፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የማ​ዝ​ዝ​ህን ሁሉ፥ በም​ስ​ክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁ​ለት ኪሩ​ቤል መካ​ከል፥ በስ​ር​የት መክ​ደ​ኛ​ውም ላይ ሆኜ እነ​ጋ​ገ​ር​ሃ​ለሁ።


በዚያ እና​ገ​ርህ ዘንድ ለአ​ንተ በም​ገ​ለ​ጥ​በት በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ለልጅ ልጃ​ችሁ የዘ​ወ​ትር መሥ​ዋ​ዕት ይሆ​ናል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ ይመ​ለ​ከት ዘንድ እንደ መጣ በአየ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከቍ​ጥ​ቋ​ጦው ውስጥ እር​ሱን ጠርቶ፥ “ሙሴ! ሙሴ!” አለው እር​ሱም፥ “ይህ ምን​ድን ነው?” አለ።


ሙሴም ድን​ኳ​ኑን ወስዶ ከሰ​ፈር ውጭ ይተ​ክ​ለው ነበር፤ ከሰ​ፈ​ሩም ራቅ ያደ​ር​ገው ነበር፤ “የም​ስ​ክ​ሩም ድን​ኳን” ብሎ ጠራው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የፈ​ለገ ሁሉ ከሰ​ፈር ውጭ ወደ​አ​ለው ወደ ድን​ኳኑ ይወጣ ነበር።


እን​ዲ​ሁም የም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ሥራ ሁሉ ተፈ​ጸመ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሁሉ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አደ​ረጉ፤ እን​ዲሁ አደ​ረጉ።


ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት የሚ​ሆ​ነ​ውን መሠ​ዊ​ያም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጅ አኖረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው በላዩ መሥ​ዋ​ዕ​ቱ​ንና ቍር​ባ​ኑን አቀ​ረበ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሲና ምድረ በዳ ቍር​ባ​ና​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ርቡ ዘንድ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ባዘዘ ጊዜ በሲና ተራራ ለሙሴ ያዘ​ዘው ይህ ነው።


የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ እንደ ሥር​ዐ​ቱም አደ​ረ​ገው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን በሲና ምድረ በዳ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ውስጥ፥ በሁ​ለ​ተ​ኛው ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን፥ ከግ​ብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት ከመ​ን​ጋ​ዎች አንድ ወይ​ፈን፥ አንድ አውራ በግ፥ አንድ የአ​ንድ ዓመት ተባት የበግ ጠቦት፤


ሙሴም ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን እር​ሱን ለመ​ነ​ጋ​ገር በገባ ጊዜ በቃል ኪዳኑ ታቦት ላይ ካለው ከስ​ር​የት መክ​ደ​ኛው በላይ ከኪ​ሩ​ቤ​ልም መካ​ከል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ድምፅ ይሰማ ነበር፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ይና​ገር ነበር።


ኦሪት በሙሴ ተሰ​ጥ​ታን ነበ​ርና፤ ጸጋና እው​ነት ግን በኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ሆነ​ልን።


ካል​ተ​ጠ​ረ​በም ድን​ጋይ ለአ​ም​ላ​ክህ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ሥራ፤ ለአ​ም​ላ​ክ​ህም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ት​ህን አቅ​ር​ብ​በት፤