የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሰቈቃወ 5:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ባሪ​ያ​ዎች ሠል​ጥ​ነ​ው​ብ​ናል፤ ከእ​ጃ​ቸ​ውም የሚ​ታ​ደ​ገን የለም።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ባሮች ሠልጥነውብናል፤ ከእጃቸው ነጻ የሚያወጣን ማንም የለም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ባርያዎች ሠልጥነውብናል፥ ከእጃቸው የሚታደገን የለም።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ባሪያዎች ይገዙናል፤ ከእጃቸውም ሊያድነን የሚችል የለም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ባሪያዎች ሠልጥነውብናል፥ ከእጃቸው የሚታደገን የለም።

ምዕራፉን ተመልከት



ሰቈቃወ 5:8
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኖኅም እን​ዲህ አለ፥ “ከነ​ዓን ርጉም ይሁን፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም የባ​ሪ​ያ​ዎች ባሪያ ይሁን።”


ሖሮ​ና​ዊ​ውም ሰን​ባ​ላጥ፥ አገ​ል​ጋ​ዩም አሞ​ና​ዊው ጦቢያ፥ ዓረ​ባ​ዊ​ውም ጌሳም በሰሙ ጊዜ በን​ቀት ሳቁ​ብን፤ ቀላል አድ​ር​ገ​ው​ንም ወደ እኛ መጡና፥ “ይህ የም​ታ​ደ​ር​ጉት ነገር ምን​ድን ነው? በውኑ በን​ጉሡ ላይ ትሸ​ፍቱ ዘንድ ትወ​ድ​ዳ​ላ​ች​ሁን?” አሉ።


ከእኔ አስ​ቀ​ድ​መው የነ​በ​ሩት አለ​ቆች ግን በሕ​ዝቡ ላይ አክ​ብ​ደው ነበር፤ ስለ እን​ጀ​ራ​ውና ስለ ወይኑ አርባ ሰቅል ብር ይወ​ስዱ ነበር፤ ሎሌ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም ደግሞ በሕ​ዝቡ ላይ ይሰ​ለ​ጥኑ ነበር። እኔ ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስለ ፈራሁ እን​ዲህ አላ​ደ​ረ​ግ​ሁም።


ከዚህ በላይ በደ​ለኛ እን​ዳ​ል​ሆ​ንሁ፥ አንተ ታው​ቃ​ለህ። ነግር ግን ከእ​ጅህ የሚ​ያ​መ​ልጥ ማን ነው?


ልጆ​ቻ​ቸው ከደ​ኅ​ን​ነት ርቀ​ዋል፥ በበ​ርም ውስጥ ይቀ​ጠ​ቅ​ጡ​አ​ቸ​ዋል፤ መከ​ራም ያጸ​ኑ​ባ​ቸ​ዋል፥ የሚ​ታ​ደ​ጋ​ቸ​ውም የለም።


ነፍ​ሴን እንደ አን​በሳ እን​ዳ​ይ​ነ​ጥ​ቋት፥ የሚ​ያ​ድ​ንና የሚ​ታ​ደግ ሳይ​ኖር።


ከጥ​ንት ጀምሮ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከእ​ጄም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም፤ እሠ​ራ​ለሁ፤ ወደ ኋላስ የሚ​መ​ልስ ማን ነው?


አሁ​ንም በወ​ዳ​ጆ​ችዋ ፊት ነው​ር​ዋን እገ​ል​ጣ​ለሁ፤ ከእ​ጄም ማንም አያ​ድ​ና​ትም።


ከእንግዲህ ወዲህ በምድር ላይ ለሚኖሩ አልራራም፥ ይላል እግዚአብሔር፣ እነሆም፥ ሰውን ሁሉ በባልንጀራውና በንጉሡ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፣ ምድሪቱም ይመታሉ፥ ከእጃቸውም አላድናቸውም።


በአ​ንተ መካ​ከል ያለ መጻ​ተኛ በአ​ንተ ላይ ከፍ ከፍ ይላል፤ አንተ ግን ዝቅ ዝቅ ትላ​ለህ።