የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሰቈቃወ 5:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ርስ​ታ​ችን ለሌላ፥ ቤቶ​ቻ​ች​ንም ለእ​ን​ግ​ዶች ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ርስታችን ለመጻተኞች፣ ቤቶቻችን ለባዕዳን ዐልፈው ተሰጡ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ርስታችን ለእንግዶች፥ ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ርስታችን ለባዕዳን ተሰጠ፤ ቤታችን ሁሉ የባዕዳን መኖሪያ ሆኖአል፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ርስታችን ለእንግዶች፥ ቤቶቻችን ለሌሎች ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት



ሰቈቃወ 5:2
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምድ​ራ​ችሁ ባድማ ናት፤ ከተ​ሞ​ቻ​ችሁ በእ​ሳት ተቃ​ጠሉ፤ እር​ሻ​ች​ሁ​ንም በፊ​ታ​ችሁ ባዕ​ዳን ይበ​ሉ​ታል፤ ጠላ​ትም ያጠ​ፋ​ዋል፤ ባድ​ማም ያደ​ር​ገ​ዋል።


የተ​ማ​ረኩ እንደ በሬ​ዎች ይሰ​ማ​ራሉ፤ የተ​ረ​ሱ​ትም ምግ​ባ​ቸ​ውን ሲፈ​ልጉ እንደ በግ ጠቦ​ቶች በማ​ሰ​ማ​ር​ያ​ቸው ይሰ​ማ​ራሉ።


በተ​ቀ​ደ​ሰው ተራ​ራህ ከር​ስ​ትህ ጥቂት ክፍል እና​ገኝ ዘንድ።


አን​ተም የሰ​ጠ​ሁ​ህን ርስት ትለ​ቅ​ቃ​ለህ፤ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም በማ​ታ​ው​ቃት ምድር ለጠ​ላ​ቶ​ችህ አስ​ገ​ዛ​ሃ​ለሁ፤ ቍጣዬ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እንደ እሳት ትነ​ድ​ዳ​ለ​ችና።


እጄን በዚች ምድር በሚ​ኖሩ ላይ እዘ​ረ​ጋ​ለ​ሁና ቤቶ​ቻ​ቸዉ፥ እር​ሻ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም፥ ሴቶ​ቻ​ቸ​ውም በአ​ን​ድ​ነት ለሌ​ሎች ይሰ​ጣሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤


በባ​ዕ​ድም እጅ ለን​ጥ​ቂያ፥ በም​ድር ኀጢ​አ​ተ​ኞ​ችም እጅ ለብ​ዝ​በዛ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ያረ​ክ​ሱ​አ​ቸ​ዋል።


ከአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ከሁሉ የሚ​ከ​ፉ​ትን አመ​ጣ​ለሁ፤ ቤታ​ቸ​ው​ንም ይወ​ር​ሳሉ፥ የኀ​ያ​ላ​ን​ንም ትዕ​ቢት አጠ​ፋ​ለሁ፤ መቅ​ደ​ሶ​ቻ​ቸ​ውም ይረ​ክ​ሳሉ።


ነፋ​ስን ዘር​ተ​ዋ​ልና ዐውሎ ነፋ​ስን አጨዱ፤ ለነ​ዶ​አ​ቸ​ውም ኀይል የለ​ውም፤ ከፍ​ሬ​ውም ዱቄት አይ​ገ​ኝም፤ ቢገ​ኝም ጠላት ይበ​ላ​ዋል።


እስ​ራ​ኤል ተው​ጦ​አል፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል ዛሬ እንደ ግትቻ ዕቃ ሆኖ​አል።


ብልጥግናቸውም ለምርኮ ይሆናል፥ ቤቶቻቸውም ይፈርሳሉ፣ ቤቶችንም ይሠራሉ፥ ነገር ግን አይቀመጡባቸውም፣ ወይንንም ይተክላሉ፥ የወይን ጠጁን ግን አይጠጡም።