የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሰቈቃወ 5:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አቤቱ፥ የሆ​ነ​ብ​ንን ዐስብ፤ ተመ​ል​ከት ስድ​ባ​ች​ን​ንም እይ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ሆይ፤ በእኛ ላይ የደረሰውን ዐስብ፤ ውርደታችንን እይ፤ ተመልከትም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አቤቱ፥ የሆነብንን አስብ፥ ተመልከት ስድባችንንም እይ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ሆይ! በእኛ ላይ የደረሰውን አስብ፤ ውርደታችንንም ተመልከት!

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አቤቱ፥ የሆነብንን አስብ፥ ተመልከት ስድባችንንም እይ።

ምዕራፉን ተመልከት



ሰቈቃወ 5:1
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነ​ር​ሱም፥ “በዚያ ስፍራ ያሉት ከም​ርኮ የተ​ረ​ፉት ቅሬ​ታ​ዎች በታ​ላቅ መከ​ራና ስድብ አሉ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ቅጥር ፈር​ሶ​አል፥ በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ተቃ​ጥ​ለ​ዋል” አሉኝ።


“አሁ​ንም ለሙሴ ለባ​ሪ​ያህ እን​ዲህ ስትል ያዘ​ዝ​ሃ​ትን ነገር አስብ። ብት​በ​ድ​ሉም በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል እበ​ት​ና​ች​ኋ​ለሁ።


አም​ላ​ካ​ችን ሆይ፥ ተን​ቀ​ና​ልና ስማ፤ ስድ​ባ​ቸ​ውን በራ​ሳ​ቸው ላይ መል​ስ​ባ​ቸው፤ በም​ርኮ ሀገር ለብ​ዝ​በዛ አሳ​ል​ፈህ ስጣ​ቸው።


ከጭቃ እንደ ፈጠ​ር​ኸኝ አስብ፤ ዳግ​መ​ኛም ወደ ትቢያ ትመ​ል​ሰ​ኛ​ለህ፤


ሕይ​ወቴ እስ​ት​ን​ፋስ እንደ ሆነች አስብ፤ ዐይ​ኔም መል​ካም ነገ​ርን ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ዳግ​መኛ አታ​ይም።


አጥ​ር​ዋን ለምን አፈ​ረ​ስህ? መን​ገድ አላ​ፊም ሁሉ ይበ​ላ​ታል።


የኀ​ያ​ላን አም​ላክ አቤቱ፥ በባ​ሪ​ያህ ጸሎት ላይ እስከ መቼ ትቈ​ጣ​ለህ?


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ጠባ​ቂ​ዎ​ች​ሽን በቅ​ጥ​ርሽ ላይ ቀንና ሌሊት አቁ​ሜ​አ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​ስቡ ከቶ ዝም አይ​ሉም፤


አቤቱ! አንተ ታው​ቃ​ለህ፤ አስ​በኝ፤ ጐብ​ኘ​ኝም፤ ከሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​ኝም አድ​ነኝ እንጂ፥ አት​ታ​ገ​ሣ​ቸው፤ ስለ አንተ እንደ ሰደ​ቡኝ አስብ።


ስድ​ባ​ች​ንን ስለ ሰማን አፍ​ረ​ናል፤ ባዕ​ዳን ሰዎ​ችም ወደ ቤተ መቅ​ደ​ሳ​ችን ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ገብ​ተ​ዋ​ልና ውር​ደት ፊታ​ች​ንን ከድ​ኖ​ታል።


ካፍ። ሕዝ​ብዋ ሁሉ እን​ጀራ አጥ​ተው ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ለማ​በ​ር​ታት ፍላ​ጎ​ታ​ቸ​ውን ስለ መብል ሰጥ​ተ​ዋል፤ አቤቱ! ተጐ​ሳ​ቍ​ያ​ለ​ሁና እይ፤ ተመ​ል​ከ​ትም።


ሬስ። አቤቱ! ተጨ​ን​ቄ​አ​ለ​ሁና፥ አን​ጀ​ቴም ታው​ኮ​ብ​ኛ​ልና ተመ​ል​ከት፤ መራራ ኀዘን አዝ​ኛ​ለ​ሁና ልቤ በው​ስጤ ተገ​ላ​በ​ጠ​ብኝ፤ በሜዳ ሰይፍ አመ​ከ​ነ​ችኝ፤ በቤ​ትም ሞት አለ።


ጤት። ግዳ​ጅዋ ከእ​ግ​ርዋ በታች ነበረ፤ ፍጻ​ሜ​ዋን አላ​ሰ​በ​ችም፤ ከባድ ሸክ​ምን ተሸ​ከ​መች፤ የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ትም የለም፤ አቤቱ! ጠላት ከፍ ከፍ ብሎ​አ​ልና መከ​ራ​ዬን ተመ​ል​ከት።


ሳም​ኬት። መን​ገድ ዐላ​ፊ​ዎች ሁሉ እጃ​ቸ​ውን ያጨ​በ​ጭ​ቡ​ብ​ሻል፦ “በውኑ የም​ድር ሁሉ ደስታ፥ አክ​ሊ​ልና ክብር የሚ​ሉ​አት ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍ​ዋ​ጫሉ፤ ራሳ​ቸ​ው​ንም ይነ​ቀ​ን​ቃሉ።


ሬስ። አቤቱ፥ እይ፤ ተመ​ል​ከት ማንን እን​ዲህ ቃረ​ምህ? በውኑ ሴቶች የማ​ኅ​ፀ​ና​ቸ​ውን ፍሬ፥ ያሳ​ደ​ጓ​ቸ​ውን ሕፃ​ናት ይበ​ላ​ሉን? በውኑ ካህ​ኑና ነቢዩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤተ መቅ​ደስ ውስጥ ይገ​ደ​ላ​ሉን?


ዛይ። ስደ​ቴ​ንና ችግ​ሬን፥ እሬ​ት​ንና ሐሞ​ትን አስብ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ ሆኖ እስ​ኪ​መ​ለ​ከት ድረስ።


ሣን። አቤቱ፥ ስድ​ባ​ቸ​ው​ንና በእኔ ላይ ያለ​ውን ዐሳ​ባ​ቸ​ውን ሁሉ ሰማህ።


አቤቱ፥ ዝናህን ሰምቼ ፈራሁ፣ አቤቱ፥ በዓመታት መካከል ሥራህን ፈጽም፣ በዓመታት መካከል ትታወቅ፣ በመዓት ጊዜ ምሕረትን አስብ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስ​ንም፥ “አቤቱ፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ትህ በመ​ጣህ ጊዜ ዐስ​በኝ” አለው።