የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 6:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሕዝ​ቡ​ንም፥ “ሂዱ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ዙሩ፤ ተዋ​ጊ​ዎ​ችም ከጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ጋር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት ይሂዱ ብላ​ችሁ እዘ​ዙ​አ​ቸው” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሕዝቡንም፣ “ወደ ፊት ሂዱ፤ ከተማዋን ዙሩ፤ የታጠቁ ተዋጊዎችም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ቀድመው ይሂዱ፤ ከተማዪቱንም ዙሩ” ሲል አዘዛቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሕዝቡንም እንዲህ አለ፦ “ሂዱ፥ ከተማይቱንም ዙሩ፥ ተዋጊዎቹም በጌታ ታቦት ፊት ይሂዱ።”

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሕዝቡንም እንዲህ ሲል አዘዘ፦ “ሂዱ፤ ከተማይቱን ዙሩ፤ ወታደሮቹም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ”።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሕዝቡንም፦ ሂዱ፥ ከተማይቱንም ዙሩ፥ ሰልፈኞችም በእግዚአብሔር ታቦት ፊት ይሂዱ አለ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 6:7
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሚስ​ቶ​ቻ​ች​ሁና ልጆ​ቻ​ችሁ ከብ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ሙሴ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ በሰ​ጣ​ችሁ በዚች ምድር ይቀ​መጡ፤ እና​ንተ፥ ጽኑ​ዓን ሁሉ ግን ታጥ​ቃ​ችሁ በወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ፊት ዮር​ዳ​ኖ​ስን ተሻ​ገሩ፤ ለእ​ነ​ር​ሱም ተዋ​ጉ​ላ​ቸው።


አርባ ሺህ ያህል ለጦ​ር​ነት የታ​ጠቁ ሰዎች የኢ​ያ​ሪ​ኮን ሀገር ይወጉ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተሻ​ገሩ።


አን​ተም ተዋ​ጊ​ዎ​ችን ሁሉ በዙ​ሪ​ያው አሰ​ል​ፋ​ቸው። ተዋ​ጊ​ዎ​ቻ​ች​ሁም ሁሉ በከ​ተ​ማ​ዪቱ ዙሪያ አንድ ጊዜ ይዙሩ፤ እን​ዲ​ሁም ስድ​ስት ቀን አድ​ርጉ።


የነ​ዌም ልጅ ኢያሱ ካህ​ና​ቱን ጠርቶ፥ “የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ከሙ፤ ሰባ​ትም ካህ​ናት ሰባት ቀንደ መለ​ከት ወስ​ደው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት ይሂዱ” አላ​ቸው።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ይሄዱ ዘንድ ኢያሱ እንደ ነገ​ራ​ቸው ሰባቱ ካህ​ናት የተ​ቀ​ደሱ ሰባ​ቱን ቀንደ መለ​ከት ይዘው ሄዱ፤ በሄ​ዱም ጊዜ አሰ​ም​ተው በም​ል​ክት ነፉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሕጉ ታቦት ትከ​ተ​ላ​ቸው ነበር።