ለሌዋውያንም ከተሞችን ትሰጣላችሁ፤ ከምትሰጡአቸውም ከተሞች ስድስቱ ነፍሰ ገዳይ የሚሸሽባቸው የመማፀኛ ከተሞች ናቸው፤ ከእነዚህ ሌላ አርባ ሁለት ከተሞችን ትሰጣላችሁ።
ኢያሱ 20:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ በሙሴ ቃል የነገርኋችሁን የመማፀኛ ከተሞችን ስጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በሙሴ በኩል በነገርኋችሁ መሠረት የመማፀኛ ከተሞች እንዲለዩ ለእስራኤላውያን ንገራቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ‘በሙሴ አማካይነት የነገርኋችሁን መማፀኛ ከተሞችን ለዩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእስራኤላውያን እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ “በሙሴ አማካይነት ባዘዝኳችሁ መሠረት የመማጠኛ ከተሞችን ለዩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ ሳይወድድ ሳያውቅም ሰውን የገደለ ገዳይ እንዲሸሽባቸው በሙሴ እጅ የነገርኋችሁን መማፀኛ ከተሞችን ለዩ፥ ከደም ተበቃዩ መማፀኛ ይሆኑላችኋል። |
ለሌዋውያንም ከተሞችን ትሰጣላችሁ፤ ከምትሰጡአቸውም ከተሞች ስድስቱ ነፍሰ ገዳይ የሚሸሽባቸው የመማፀኛ ከተሞች ናቸው፤ ከእነዚህ ሌላ አርባ ሁለት ከተሞችን ትሰጣላችሁ።
ባለማወቅ ሳይወድድ ሰውን የገደለ በዚያ ይማፀን ዘንድ፥ ለእናንተ የመማፀኛ ከተሞችን ሥሩ፤ ነፍስ የገደለ ሰውም በአደባባይ ለፍርድ እስኪቀርብ ድረስ በደም ተበቃዩ አይገደል።