የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኢያሱ 17:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለኦ​ፌር ልጅ፥ ለሰ​ለ​ጰ​ዓድ ግን ሴቶች ልጆች እንጂ ወን​ዶች ልጆች አል​ነ​በ​ሩ​ትም፤ የሰ​ለ​ጰ​ዐ​ድም የሴ​ቶች ልጆቹ ስሞች፦ መሐላ፥ ኑዓ፥ ሔግላ፥ ሚልካ፥ ቴርሳ ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሰለጰዓድ የአፌር ልጅ፣ የገለዓድ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የምናሴ ልጅ ነው። እርሱም ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም። የሴቶች ልጆቹም ስም ማህለህ፣ ኑዓ፣ ዔግላ፣ ሚልካ፣ ቲርጻ ይባላል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለምናሴ ልጅ፥ ለማኪር ልጅ፥ ለገለዓድ ልጅ፥ ለኦፌር ልጅ፥ ለሰለጰዓድ ግን ሴቶች ልጆች ብቻ እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም የሴቶች ልጆቹም ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጸለጰሐድ የሔፌር ልጅ፥ ሔፌር የገለዓድ ልጅ፥ ገለዓድ የማኪር ልጅ፥ ማኪርም የምናሴ ልጅ ነው፤ ታዲያ ይህ ጸለጰሐድ ሴቶች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም፤ አምስቱ ሴቶች ልጆቹም ማሕላ፥ ኖዓ፥ ሖግላ፥ ሚልካ እና ቲርጻ ተብለው ይጠሩ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለምናሴ ልጅ፥ ለማኪር ልጅ፥ ለገለዓድ ልጅ፥ ለኦፌር ልጅ፥ ለሰለጰዓድ ግን ሴቶች ልጆች እንጂ ወንዶች ልጆች አልነበሩትም የሴቶች ልጆቹም ስም ማህለህ፥ ኑዓ፥ ዔግላ፥ ሚልካ፥ ቲርጻ ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኢያሱ 17:3
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዮሴ​ፍም የኤ​ፍ​ሬ​ምን ልጆች እስከ ሦስት ትው​ልድ አየ። የም​ናሴ ልጅ የማ​ኪር ልጆ​ችም በዮ​ሴፍ ጭን ላይ ተወ​ለዱ።


የም​ናሴ ልጆች፤ ከማ​ኪር የማ​ኪ​ራ​ው​ያን ወገን፤ ማኪ​ርም ገለ​ዓ​ድን ወለደ፤ ከገ​ለ​ዓድ የገ​ለ​ዓ​ዳ​ው​ያን ወገን።


ከዮ​ሴፍ ልጅ ከም​ናሴ ወገን ፥ የም​ናሴ ልጅ፥ የማ​ኪር ልጅ፥ የገ​ለ​አድ ልጅ፥ የኦ​ፌር ልጅ፥ የሰ​ለ​ጰ​ዓድ ሴቶች ልጆች መጡ፤ የእ​ነ​ዚ​ህም ሴቶች ልጆች ስሞች መሐላ፥ ኑኃ፥ ሄግላ፥ ሚልካ፥ ቴርሳ ነበሩ።


ዕጣ​ውም ለቀ​ሩት ለም​ናሴ ልጆች በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው፥ ለኢ​ያ​ዜር ልጆች፥ ለቄ​ሌዝ ልጆች፥ ለኢ​የ​ዚ​ኤል ልጆች፥ ለሴ​ኬም ልጆች፥ ለሱ​ማ​ሪም ልጆች፥ ለኦ​ፌር ልጆች ሆነ፤ ወን​ዶቹ በየ​ወ​ገ​ኖ​ቻ​ቸው እነ​ዚህ ናቸው።