ላባም አለው፥ “እኛ አንዳችን ከሌላው እንለያያለንና ራእይን የገለጠልኝ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ሆኖ ይመልከት።
ኢያሱ 13:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሐሴቦን ጀምሮ እስከ አራቦት መሴፋ፥ እስከ ቦጣኒም ድረስ፥ ከማኦን ጀምሮ እስከ ዴቦን ዳርቻ ድረስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሐሴቦን እስከ ራማት ምጽጳና ከዚያም እስከ ብጦኒም፣ ከመሃናይም እስከ ደቤር ግዛት ያለውን፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከሐሴቦን ጀምሮ እስከ ራማት ምጽጴ፥ እስከ ብጦኒም ድረስ፥ ከመሃናይም ጀምሮ እስከ ዳቤር ዳርቻ ድረስ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምድራቸውም ስፋት ከሐሴቦን ተነሥቶ እስከ ራማት ምጽጳና እስከ ቤጦኒም እንዲሁም ከማሕናይም ተነሥቶ እስከ ሎዴባር ድንበር ይደርሳል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከሐሴቦን ጀምሮ እስከ ራማት ምጽጴ፥ እስከ ብጦኒም ድረስ፥ ከመሃናይም ጀምሮ እስከ ዳቤር ዳርቻ ድረስ፥ |
ላባም አለው፥ “እኛ አንዳችን ከሌላው እንለያያለንና ራእይን የገለጠልኝ እግዚአብሔር በእኔና በአንተ መካከል ሆኖ ይመልከት።
ዳዊትም ወደ ምናሄም በመጣ ጊዜ በአሞን ልጆች ሀገር በአራቦት የነበረ የነዓሶን ልጅ ኡኤሴብ፥ የሎዶባርም ሰው የአሜሄል ልጅ ማኪር፥ የሮጌሌምም ሰው ገለዓዳዊው ቤርዜሊ፥
የእስራኤልም ንጉሥ አገልጋዮቹን፥ “ሬማት ዘገለዓድ የእኛ እንደ ሆነች፥ እኛም ከሶርያ ንጉሥ እጅ ሳንወስዳት ዝም እንዳልን ታውቃላችሁን?” አላቸው።
ድንበራቸውም ኢያዜርና የገለዓድ ከተሞች ሁሉ፥ የአሞንም ልጆች ምድር እኩሌታ በራባት ፊት እስካለችው እስከ አሮዔር ድረስ፥
በሸለቆውም ቤትሀራም፥ ቤትንምራ፥ ሱኮት፥ ጻፎን፥ የሐሴቦን ንጉሥ የሴዎን መንግሥት ቅሬታ ነበረ። ድንበሩም ዮርዳኖስና በምሥራቅ በኩል ባለው በዮርዳኖስ ማዶ የኬኔሬት ባሕር ወዲያኛው ዳርቻ ነበረ።
በዮርዳኖስም ማዶ ከኢያሪኮ ወደ ምሥራቅ ከሮቤል ነገድ በምድረ በዳው በደልዳላው ስፍራ ቦሶርን፥ ከጋድም ነገድ በገለዓድ ኤርሞትን፥ ከምናሴም ነገድ በባሳን ጎላንን ለዩ።
ከጋድም ነገድ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን በገለዓድ ውስጥ ራሞትንና መሰማርያዋን፥ ቃሚንንና መሰማርያዋን፤
ዮፍታሔም ከገለዓድ ሽማግሌዎች ጋር ሄደ፤ ሕዝቡም መስፍን ይሆናቸው ዘንድ በላያቸው አለቃ አድርገው ሾሙት፤ ዮፍታሔም ቃሉን ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት በመሴፋ ተናገረ።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በዮፍታሔ ላይ መጣ፤ እርሱም የምናሴ ዕጣ ከምትሆን ከገለዓድ ምድርና ከገለዓድ መሴፋ፥ ወደ አሞን ልጆች ማዶ ተሻገረ።