ወደ ከተማም ቢገባ እስራኤል ሁሉ ወደዚያች ከተማ ገመድ ይወስዳሉ፤ እኛም አንድ ድንጋይ እንኳን እስከማይገኝባት ድረስ ወደ ወንዙ ውስጥ እንስባታለን።”
ኢያሱ 10:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ ግን አትዘግዩ፤ ጠላቶቻችሁንም እስከ መጨረሻው ተከታትላችሁ ያዙአቸው፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና ወደ ከተሞቻቸው እንዳይገቡ ከልክሉአቸው፤” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠላቶቻችሁን አሳድዷቸው እንጂ ችላ አትበሉ፤ ከበስተ ኋላ ሆናችሁም አደጋ ጣሉባቸው፤ ወደ ከተሞቻቸው እንዳይገቡ ከልክሏቸው፤ እነሆ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቷቸዋልና።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ ግን አትዘግዩ፥ ጠላቶቻችሁንም አሳድዷቸው፥ ከኋላ በኩል እየተከተላችሁም ምቱአቸው፤ አምላካችሁም ጌታ በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና ወደ ከተሞቻቸው እንዳይገቡ ከልክሉአቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ግን በዚያ አትቈዩ፤ ጠላትን እያሳደዳችሁ ከኋላ በኩል አደጋ መጣላችሁን ቀጥሉ፤ ሸሽተው ወደ ከተሞቻቸው እንዲገቡ መንገድ አትስጡአቸው! አምላካችሁ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ድልን ያቀዳጃችኋልና።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ ግን አትዘግዩ፥ ጠላቶቻችሁንም አባርሩአቸው፥ በኋላም ያሉትን ግደሉ፥ አምላካችሁም እግዚአብሔር በእጃችሁ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋልና ወደ ከተሞቻቸው እንዳይገቡ ከልክሉአቸው አለ። |
ወደ ከተማም ቢገባ እስራኤል ሁሉ ወደዚያች ከተማ ገመድ ይወስዳሉ፤ እኛም አንድ ድንጋይ እንኳን እስከማይገኝባት ድረስ ወደ ወንዙ ውስጥ እንስባታለን።”
ዳዊትም አቢሳን፥ “አሁን አቤሴሎም ከአደረገብን ይልቅ የከፋ የሚያደርግብን የቢኮሪ ልጅ ሳቡሄ ነው፤ እርሱ የተመሸጉትን ከተሞች አግኝቶ ከዐይናችን እንዳይሰወር፥ አንተ የጌታህን ብላቴኖች ወስደህ አሳድደው” አለው።
“ዝም ብለን ለምን እንቀመጣለን? እግዚአብሔርን ስለ በደልን አምላካችን እግዚአብሔር አጥፍቶናልና፥ የሐሞትንም ውኃ አጠጥቶናልና ተሰብስባችሁ ወደ ተመሸጉ ከተሞች እንግባ በዚያም እንጥፋ።
እስኪጠፉም ድረስ ኢያሱና የእስራኤል ልጆች በታላቅ መምታት መምታታቸውን በፈጸሙ ጊዜ፥ ከእነርሱም ያመለጡት ወደ ተመሸገ ከተማ በገቡ ጊዜ፥