ኢያሱ 10:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒቤዜቅ ኢያሱ ጋይን እንደ ያዘ፥ ፈጽሞም እንዳጠፋት፥ በኢያሪኮና በንጉሥዋም ያደረገውን እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋም እንዳደረገ፥ የገባዖንም ሰዎች ከኢያሱና ከእስራኤል ጋር ሰላም እንዳደረጉ፥ በመካከላቸውም እንደ ሆኑ በሰማ ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ፣ ኢያሱ ጋይን ይዞ እንደ ደመሰሳት፣ እንደዚሁም በኢያሪኮና በንጉሧ ላይ ያደረገውን ሁሉ፣ በጋይና በንጉሧ ላይ ማድረጉን፣ የገባዖን ሰዎችም ከእስራኤል ጋራ የሰላም ውል አድርገው በአጠገባቸው መኖራቸውን ሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም ሆነ፤ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ኢያሱ ጋይን እንደ ያዘ ፈጽሞም እንዳጠፋት፥ በኢያሪኮና በንጉሥዋም ያደረገውን እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋ እንዳደረገ፥ የገባዖንም ሰዎች ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት አድርገው በመካከላቸውም እንደ ሆኑ በሰማ ጊዜ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢያሱ የዐይን ከተማ በጦርነት ከያዘ በኋላ በኢያሪኮና በንጉሥዋ ላይ ባደረገው ዐይነት በፍጹም የደመሰሳት መሆኑንና ንጉሥዋንም መግደሉን የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ሰማ፤ እንዲሁም የገባዖን ሰዎች ከእስራኤላውያን ጋር ስምምነት አድርገው በሰላም መኖራቸውን ተረዳ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፥ የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒጼዴቅ ኢያሱ ጋይን እንደ ያዘ ፈጽሞም እንዳጠፋት፥ በኢያሪኮና በንጉሥዋም ያደረገውን እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋ እንዳደረገ፥ የገባዖንም ሰዎች ከእስራኤል ጋር ሰላም እንዳደረጉ በመካከላቸውም እንደ ሆኑ በሰማ ጊዜ፥ |
የሳሌም ንጉሥ፥ የልዑል እግዚአብሔርም ካህን የሆነ፥ ይህ መልከ ጼዴቅ፥ አብርሃም ነገሥታትን ድል ነሥቶ በተመለሰ ጊዜ ከእርሱ ጋር ተገናኝቶ ባረከው።
ስለዚህም የኢየሩሳሌም ንጉሥ አዶኒቤዜቅ ወደ ኬብሮን ንጉሥ ወደ ኤላም፥ ወደ የርሙት ንጉሥም ወደ ፊዶን፥ ወደ ለኪስ ንጉሥም ወደ ኤፍታ፥ ወደ አዶላም ንጉሥም ወደ ዳቤር ልኮ፥
ኢያሱም ከተማዋን፥ በከተማዪቱም ውስጥ የነበሩትን ሁሉ፥ ከወንድ እስከ ሴት፥ ከሕፃን እስከ ሽማግሌ፥ ከበሬ እስከ በግና እስከ አህያ በሰይፍ ስለት ፈጽሞ አጠፋ።
በኢያሪኮና በንጉሥዋም እንዳደረግህ እንዲሁ በጋይና በንጉሥዋ ታደርጋለህ፤ የከብቱን ምርኮ ግን ለራሳችሁ ትዘርፋላችሁ፤ ከከተማዪቱም በስተኋላ ይከብቧት ዘንድ ጦር ላክ” አለው።
ኢያሱ፥ እስራኤልም ሁሉ ተደብቀው የነበሩት ከተማዪቱን እንደ ያዙ፥ የከተማዪቱም ጢስ ወደ ሰማይ ሲወጣ ባዩ ጊዜ ወደኋላ ተመልሰው የጋይን ሰዎች ገደሉአቸው።