የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዮሐንስ 20:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጐን​በስ ብሎም ሲመ​ለ​ከት በፍ​ታ​ዉን ተቀ​ምጦ አየ፤ ነገር ግን ወደ ውስጥ አል​ገ​ባም።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ጐንበስ ብሎ ወደ ውስጥ ሲመለከት፣ በፍታውን ብቻ ተቀምጦ አየ፤ ወደ መቃብሩ ግን አልገባም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዝቅም ብሎ ሲመለከት የተልባ እግሩን ልብስ ተቀምጦ አየ፤ ነገር ግን አልገባም።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጐንበስ ብሎም ወደ መቃብሩ ቢመለከት የከፈኑ ጨርቅ እዚያ ተቀምጦ አየ፤ ነገር ግን ወደ ውስጥ አልገባም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዝቅም ብሎ ቢመለከት የተልባ እግሩን ልብስ ተቀምጦ አየ፥ ነገር ግን አልገባ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዮሐንስ 20:5
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሞቶ የነ​በ​ረ​ውም እንደ ተገ​ነዘ፥ እጁ​ንና እግ​ሩ​ንም እንደ ታሰረ፥ ፊቱም በሰ​በን እንደ ተጠ​ቀ​ለለ ወጣ፤ ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “እን​ግ​ዲ​ህስ ፍቱ​ትና ተዉት ይሂድ” አላ​ቸው።


እንደ አይ​ሁድ አገ​ና​ነዝ ሥር​ዐ​ትም የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱ​ስን ሥጋ ወስ​ደው ከሽቱ ጋር በበ​ፍታ ገነ​ዙት።


ማር​ያም ግን ከመ​ቃ​ብሩ በስ​ተ​ውጭ እያ​ለ​ቀ​ሰች ቆማ ነበረ፤ እያ​ለ​ቀ​ሰ​ችም ወደ መቃ​ብሩ ጐን​በስ ብላ ተመ​ለ​ከ​ተች።


ሁለ​ቱም በአ​ን​ድ​ነት ሲሮጡ ያ ሌላዉ ደቀ መዝ​ሙር ጴጥ​ሮ​ስን ቀድ​ሞት ወደ መቃ​ብሩ ደረሰ።


ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም ተከ​ት​ሎት ደረ​ሰና ወደ መቃ​ብሩ ገባ፤