ኤርምያስ 51:60 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሠራያም የቤቱ አዛዥ ነበረ፤ በባቢሎንም ላይ የሚመጣውን ክፉ ነገር ሁሉ፥ ስለ ባቢሎን የተጻፈውን ይህን ቃል ሁሉ ኤርምያስ በአንድ መጽሐፍ ላይ ጻፈው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስ ስለ ባቢሎን ጽፎ ያስቀመጠውን ሁሉ፣ በባቢሎን ላይ የሚመጣውን ጥፋት ሁሉ በብራና ጥቅልል ላይ ጻፈው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በባቢሎንም ላይ የሚመጣውን ክፉ ነገር ሁሉ፥ ስለ ባቢሎን የተጻፈውን ይህን ቃል ሁሉ፥ ኤርምያስ በመጽሐፍ ላይ ጻፈው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በባቢሎን ላይ የሚመጣውን ጥፋት እንዲሁም ስለ እርስዋ የተነገረውን ቃል በመጽሐፍ ጻፍኩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በባቢሎንም ላይ የሚመጣውን ክፉ ነገር ሁሉ፥ ስለ ባቢሎን የተጻፈውን ይህን ቃል ሁሉ፥ ኤርምያስ በመጽሐፍ ላይ ጻፈው። |
ኤርምያስም ሌላ ክርታስ ወሰደ፤ ለኔርዩም ልጅ ለጸሓፊው ለባሮክ ሰጠው፤ እርሱም የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአቄም በእሳት ያቃጠለውን የመጽሐፉን ቃል ሁሉ ከኤርምያስ አፍ ጻፈበት፤ ደግሞም እንደ ቀድሞው ያለ ቃል ብዙ ቃል ተጨመረበት።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ በባቢሎን ላይና በከለዳውያን ምድር በሚኖሩት ላይ የሚያቃጥልና የሚያጠፋ ነፋስን አስነሣለሁ።
እንዲሁም “የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊላደልፊያም ወደ ሎዲቅያም በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ፤” አለኝ።