የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 50:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከባ​ቢ​ሎን መካ​ከል ሽሹ፤ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ምድር ውጡ፤ በበ​ጎ​ችም ፊት እንደ እባ​ቦች ሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ከባቢሎን ሽሹ፤ የባቢሎናውያንን ምድር ልቀቁ፤ መንጋ እንደሚመራ የፍየል አውራ ሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከባቢሎን መካከል ሽሹ፥ ከከለዳውያንም ምድር ውጡ፥ በመንጎችም ፊት እንደ አውራ ፍየሎች ሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ከባቢሎን ሸሽታችሁ ውጡ! አገሪቱን ለቃችሁ ሂዱ! መንጋውን እንደሚመራ የፍየል አውራ ሁኑ!

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከባቢሎን መካከል ሽሹ፥ ከከለዳውያንም ምድር ውጡ፥ በመንጎችም ፊት እንደ አውራ ፍየሎች ሁኑ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 50:8
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከባ​ቢ​ሎን ውጡ፤ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ኰብ​ልሉ፤ በእ​ል​ልታ ድምፅ ተና​ገሩ፤ ይህም ይሰማ፤ እስከ ምድ​ርም ዳርቻ ድረስ አው​ሩና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባር​ያ​ውን ያዕ​ቆ​ብን ታድ​ጎ​ታል” በሉ።


ጽዮን ሆይ፥ ተነሺ፥ ተነሺ፤ ጽዮን ሆይ፥ ኀይ​ል​ሽን ልበሺ፤ አን​ቺም ቅድ​ስ​ቲቱ ከተማ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ያል​ተ​ገ​ረ​ዘና ርኩስ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ወደ አንቺ አያ​ል​ፍ​ምና ክብ​ር​ሽን ልበሺ።


እና​ንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ዕቃ የም​ት​ሸ​ከሙ ሆይ፥ እልፍ በሉ፤ እልፍ በሉ፤ ከዚያ ውጡ፤ ርኩ​ስን ነገር አት​ንኩ፤ ከመ​ካ​ከ​ልዋ ውጡ፤ ራሳ​ች​ሁን ለዩ።


“ሕዝቤ ሆይ! ከመ​ካ​ከ​ልዋ ውጡ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽኑ ቍጣ ራሳ​ች​ሁን አድኑ።


ከባ​ቢ​ሎን መካ​ከል ሽሹ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም ነፍ​ሳ​ች​ሁን አድኑ፤ በበ​ደ​ልዋ አት​ጥፉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀል ጊዜ ነውና፥ እር​ሱም ብድ​ራ​ቷን ይከ​ፍ​ላ​ታ​ልና።


በዚያም ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፥ ሕዝብም ይሆኑኛል፣ በመካከልሽም እኖራለሁ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ አንቺ እንደ ላከኝ ታውቂአለሽ።


ማኅ​በ​ሩ​ንም፥ “ከእ​ነ​ዚህ ክፉ​ዎች ሰዎች ድን​ኳን ፈቀቅ በሉ፤ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ እን​ዳ​ት​ጠፉ ለእ​ነ​ርሱ የሆ​ነ​ውን ሁሉ አት​ንኩ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።


ስለ​ዚ​ህም “ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ተለ​ይ​ታ​ችሁ ውጡ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩ​ሳ​ንም አት​ቅ​ረቡ፥ እኔም እቀ​በ​ላ​ች​ኋ​ለሁ።


ከሰማይም ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ “ሕዝቤ ሆይ! በኀጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤