ምድርን ጐበኘሃት አረካሃትም፥ ብልጽግናዋንም እጅግ አበዛህ፤ የእግዚአብሔር ወንዝ ውኆችን የተመላ ነው፤ ምግባቸውን አዘጋጀህ፥ እንዲሁ ታሰናዳለህና።
ኤርምያስ 50:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለአሕዛብ ተናገሩ፤ አውሩም፤ ዓላማውንም አንሡ፥ አትደብቁ፦ ባቢሎን ተያዘች፤ ቤል አፈረ፤ ሜሮዳክ ፈራች፤ ምስሎችዋም አፈሩ፤ ጣዖታቷም ደነገጡ፤ በሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “በሕዝቦች መካከል ተናገሩ፤ አስታውቁም፤ ሰንደቅ ዐላማ አንሡ፤ ዐውጁ፤ አንዳች ሳታስቀሩ፣ እንዲህ በሉ፤ ‘ባቢሎን ትያዛለች፤ ቤል ይዋረዳል፤ ሜሮዳክ በሽብር ይሞላል፤ ጣዖቶቿ ይዋረዳሉ፤ አማልክቷም ይሸበራሉ።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአሕዛብ መካከል ተናገሩ አውጁም፥ ዓላማውንም አንሡ፤ አውጁ፥ ሳትደብቁም እንዲህ በሉ፦ ባቢሎን ተያዘች፥ ቤል አፈረ፥ ሜሮዳክ ተሰባበረ፤ ምስሎችዋ አፈሩ፥ ጣዖታትዋ ተሰባበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ለአሕዛብ ሁሉ በማወጅ ወሬውን ንገሩ! አርማ አንሥታችሁ ዜናውን አስታውቁ! ከቶ ምሥጢር አድርጋችሁ አታስቀሩ! እነሆ ባቢሎን ተያዘች፤ ቤል የተባለው ጣዖት እንዲያፍር ተደረገ፤ ‘ማርዱክ’ የተባለ ጣዖቷም ተሰባብሮአል፤ የባቢሎን ጣዖቶች አፍረዋል፤ አጸያፊ ምስሎችዋም ተሰባብረዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአሕዛብ መካከል ተናገሩ አውሩም፥ ዓላማውንም አንሡ፥ አውሩ፥ አትደብቁ፦ ባቢሎን ተወሰደች፥ ቤል አፈረ፥ ሜሮዳክ ደነገጠ፥ ምስሎችዋ አፈሩ፥ ጣዖታትዋ ደነገጡ በሉ። |
ምድርን ጐበኘሃት አረካሃትም፥ ብልጽግናዋንም እጅግ አበዛህ፤ የእግዚአብሔር ወንዝ ውኆችን የተመላ ነው፤ ምግባቸውን አዘጋጀህ፥ እንዲሁ ታሰናዳለህና።
በዚያም ቀን እንዲህ ትላላችሁ፥ “እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ስሙንም ጥሩ፤ በአሕዛብ መካከል ክብሩን አስታውቁ፤ ስሙ ከፍ ያለ እንደ ሆነ አስታውሱ።
እነሆም፥ በፈረሶች የሚቀመጡ፥ ሁለት ሁለት ሆነው የሚሄዱ ፈረሰኞች ይመጣሉ” ብሎ ጮኸ፤ እርሱም መልሶ፥ “ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! ጣዖቶችዋም ሁሉ፥ የእጆችዋም ሥራዎች ሁሉ በምድር ላይ ተጥለው ደቀቁ” አለ።
አማልክቶቻቸውንም በእሳት አቃጥለዋል፤ የእንጨትና የድንጋይ የሰው እጅ ሥራም ነበሩ እንጂ አማልክት አልነበሩምና ስለዚህ አጥፍተዋቸዋል።
በዚያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ የባልዳን ልጅ መሮዳክ ባልዳን ሕዝቅያስ ታምሞ እንደ ተፈወሰ ሰምቶ ነበርና ደብዳቤና እጅ መንሻን፥ መልእክተኞችንም ላከለት።
ቤል ወደቀ፤ ዳጎን ተሰባበረ፤ ምስሎቻቸውም እንደ ትቢያ ሆኑ፤ አራዊትና እንስሳም ይረግጡአቸዋል፤ እንደ ፋንድያም ሸክም የሚያጸይፉ ናቸውና አያነሡአቸውም።
ከባቢሎን ውጡ፤ ከከለዳውያንም ኰብልሉ፤ በእልልታ ድምፅ ተናገሩ፤ ይህም ይሰማ፤ እስከ ምድርም ዳርቻ ድረስ አውሩና፥ “እግዚአብሔር ባርያውን ያዕቆብን ታድጎታል” በሉ።
እናንተም፦ ሰማይንና ምድርን ያልፈጠሩ እነዚህ አማልክት ከምድር ላይ፥ ከሰማይም በታች ፈጽመው ይጥፉ ትሉአቸዋላችሁ።
አሕዛብ ሆይ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ በሩቅም ላሉ ደሴቶች አውሩና፥ “እስራኤልን የበተነ እርሱ ይሰበስበዋል፤ እረኛም መንጋውን እንደሚጠብቅ ይጠብቀዋል በሉ።
ለአሕዛብ አሳስቡ፥ “እነሆ፥ መጡ! ጠላቶች ከሩቅ ሀገር ይመጣሉ፤ በይሁዳም ከተሞች ላይ ይጮኻሉ ብላችሁ በኢየሩሳሌም ላይ አውጁ።
“በግብፅ ተናገሩ፤ በሚግዶልም አውሩ፤ በሜምፎስና በጣፍናስ አሰሙ፤ ሰይፍ በዙሪያህ ያለውን በልቶአልና፦ ተነሥ ተዘጋጅም በሉ።
በባቢሎን ቅጥሮች ላይ ዓላማውን አንሡ፤ ከጕራንጕሬአችሁ ጋር ጽኑ፤ ተመልካቾችን አቁሙ፤ መሣሪያችሁን አዘጋጁ። እግዚአብሔር በባቢሎን በሚኖሩት ላይ የተናገረውን ያደርግ ዘንድ ጀምሮአልና።
“በምድር ላይ ዓላማን አንሡ፤ በአሕዛብም መካከል መለከትን ንፉ፤ አሕዛብንም ለዩባት፤ የአራራትንና የሚኒን የአስከናዝንም መንግሥታት እዘዙባት፤ ጦረኞችንም በላይዋ አቁሙ፤ ብዛታቸው እንደ አንበጣ የሆኑ ፈረሶችን በላይዋ አውጡ።
ለባቢሎን ንጉሥ ይነግር ዘንድ ሯጩ ሯጩን ለመገናኘት፤ መልእክተኛውም መልእክተኛውን ለመገናኘት ይሮጣል፤ ከተማዋ ከዳር እስከ ዳር ተይዛለችና፤
በባቢሎንም ላይ እበቀላለሁ፤ የዋጠችውንም ከአፍዋ አስተፋታለሁ፤ አሕዛብም ከዚያ ወዲያ ወደ እርስዋ አይሰበሰቡም፤ የባቢሎንም ቅጥሮች ይወድቃሉ።
ስለዚህ እነሆ የተቀረጹትን የባቢሎንን ምስሎች የምበቀልበት ዘመን ይመጣል፤ ምድርዋም ሁሉ ትደርቃለች፤ ተዋግተውም የሞቱት ሁሉ በመካከልዋ ይወድቃሉ።
ስለዚህ እነሆ የተቀረጹትን ምስሎችዋን የምበቀልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በምድርዋም ሁሉ የተገደሉት ይወድቃሉ።
እንዲህም ሆነ፤ የይሁዳ ንጉሥ ኢኮንያን በተማረከ በሠላሳ ሰባተኛው ዓመት፥ በዐሥራ ሁለተኛው ወር ከወሩም በሃያ አምስተኛው ቀን፥ የባቢሎን ንጉሥ ዮርማሮዴቅ በነገሠ በአንደኛው ዓመት የይሁዳን ንጉሥ የኢኮንያንን ራስ ከፍ ከፍ አደረገ፤ ከወህኒም አወጣው፤
እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርንም አማልክት ሁሉ ያከሳቸዋል፣ በአሕዛብም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በስፍራቸው ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።
በብርቱም ድምፅ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፤ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤