የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 48:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

መፍ​ረ​ስና ታላቅ ጥፋት የሚል የጩ​ኸት ቃል ከሖ​ሮ​ና​ይም ተሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከሖሮናይም የሚወጣውን ጩኸት፣ የመውደምና የታላቅ ጥፋት ድምፅ ስሙ!

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

መፍረስና ታላቅ ጥፋት፥ የሚል የጩኸት ድምፅ ከሖሮናይም ተሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በሖሮናይም ላይ በሚደርሰው ውድመትና ጥፋት የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

መፍረስና ታላቅ ጥፋት የሚል የጩኸት ቃል ከሖሮናይም ተሰማ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 48:3
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለራ​ሳ​ችሁ እዘኑ፤ ጣዖ​ታ​ች​ሁና መሠ​ዊ​ያ​ችሁ ያሉ​ባት ዲቦን ትጠ​ፋ​ለ​ችና፤ ወደ​ዚ​ያም ወጥ​ታ​ችሁ በሞ​ዓብ ናባው አል​ቅሱ፤ ወዮም በሉ፤ ራስ ሁሉ በራ ይሆ​ናል፤ ክን​ድም ሁሉ ይቈ​ረ​ጣል።


ሞዓብ ራሷን ይዛ ትጮ​ኻ​ለች፤ ለል​ቧም ይረ​ዳ​ታል፤ እስከ ሴጎ​ርም ድረስ ብቻ​ዋን ታለ​ቅ​ሳ​ለች። ሞዓብ እንደ ሦስት ዓመት ጥጃ ናትና በሉ​ሒት ዐቀ​በት ትጮ​ኻ​ለች። በአ​ሮ​ሜ​ዎን መን​ገ​ድም ይመ​ለ​ሳሉ፤ ይጮ​ኻ​ሉም፥ ጥፋ​ትና መና​ወ​ጥም ይሆ​ናል።


ጩኸት የሞ​ዓ​ብን ዳርቻ ሁሉ ዞረ፤ ልቅ​ሶ​ዋም ወደ ኤግ​ላ​ይ​ምና ወደ ኢሊም ጕድ​ጓድ ደረሰ።


ስለ​ዚህ፥ “ተዉኝ እኔ መራራ ልቅሶ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ጥፋ​ትም ታጽ​ና​ኑኝ ዘንድ አት​ድ​ከሙ፥” አልሁ።


ያም ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቍ​ጣው እንደ ገለ​በ​ጣ​ቸው፥ ይቅ​ርም እንደ አላ​ላ​ቸው ከተ​ሞች ይሁን፥ በማ​ለ​ዳም ልቅ​ሶን፥ በቀ​ት​ርም ጩኸ​ትን ይስማ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ ውኃ ከሰ​ሜን ይነ​ሣል፥ የሚ​ያ​ጥ​ለ​ቀ​ል​ቅም ፈሳሽ ይሆ​ናል፤ በሀ​ገ​ሪ​ቱና በመ​ላዋ ሁሉ፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱና በሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም ላይ ይጐ​ር​ፋል፤ ሰዎ​ቹም ይጮ​ኻሉ፤ በም​ድ​ርም የሚ​ኖሩ ሁሉ ያለ​ቅ​ሳሉ።


ከሐ​ሴ​ቦን ጩኸት እስከ ኤሊ​ያ​ሊና እስከ ኢያሳ ድረስ ድም​ፃ​ቸ​ውን ሰጥ​ተ​ዋል፤ ከሴ​ጎር እስከ ሖሮ​ና​ይ​ምና እስከ ዔግ​ላት ሺሊ​ሺያ ድረስ ይደ​ር​ሳል፤ የኔ​ም​ሬም ውኃ ደር​ቋ​ልና።


ሞአብ ጠፍ​ታ​ለች፤ ይህ​ንም በሴ​ጎር ተና​ገሩ።


በሎ​ዊት ዓቀ​በት ልቅሶ እያ​ለ​ቀሱ ይወ​ጣ​ሉና፥ በሖ​ሮ​ና​ይ​ምም መን​ገድ የመ​ባ​ባ​ትን ጩኸት ሰም​ተ​ዋል።


“ከባ​ቢ​ሎን የጩ​ኸት ድምፅ፥ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ምድር የታ​ላቅ ጥፋት ድምፅ ተሰ​ም​ቶ​አል።