ኤርምያስ 48:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተ፦ እኛ ኀያላን በሰልፍም ጽኑዓን ነን እንዴት ትላላችሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ፣ ‘እኛ ተዋጊዎች ነን፤ በጦርነትም ብርቱ ነን’ ልትሉ እንዴት ቻላችሁ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተ፦ እኛ ኃያላን በውጊያም ጽኑዓን ነን፥ እንዴት ትላላችሁ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የሞአብ ሰዎች ሆይ! ‘እኛ ተዋጊ አርበኞችና በጦርነት የተፈተንን ወታደሮች ነን’ ብላችሁ ስለምን ትመካላችሁ? አጥፊው መጥቶአል፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተ፦ እኛ ኃያላን በሰልፍም ጽኑዓን ነን እንዴት ትላላችሁ? |
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሓይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ጦርነትም ለኀያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለዐዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ያገናኛቸዋል።
እርሱ እንዲህ ብሎአልና፥ “በኀይሌ አደርጋለሁ፤ በማስተዋል ጥበቤም የአሕዛብን ድንበሮች አርቃለሁ፤ ሀብታቸውንም እዘርፋለሁ፤
ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በክብርህ ላይ ውርደትን፥ በጌጥህ ላይም የሚነድና የሚያቃጥል እሳትን ይሰድዳል።
የሞዓብን ትዕቢትና እጅግ መኵራቱን ሰምተናል፤ ትዕቢቱንም አስወገድሁ፤ ጥንቈላህ እንዲህ አይደለምና፥ እንዲህም አይደለም፤
በዓለት ንቃቃት ውስጥ የምትቀመጥ፥ የተራራውን ከፍታ የምትይዝ ሆይ! ድፍረትህና የልብህ ኵራት አነሣሥተውሃል። ቤትህንም ምንም እንደ ንስር ከፍ ብታደርግ፥ ከዚያ አወርድሃለሁ፥” ይላል እግዚአብሔር።
“እናንተስ፦ ጥበበኞች ነን የእግዚአብሔርም ሕግ ከእኛ ጋር ነው እንዴት ትላላችሁ? እነሆ ጸሓፊዎቻቸውም ከንቱ ሆኑ፤ በሐሰትም ብርዕ ተጠቀሙ።
“እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ ግብፅን የሚደግፉ ይወድቃሉ፤ የኀይልዋም ትዕቢት ይወርዳል፤ ከሚግዶል ጀምሮ እስከ ሰዌኔ ድረስ በእርስዋ ውስጥ በሰይፍ ይወድቃሉ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።