እስማኤልም ከጎዶልያስ ጋር በመሴፋ የነበሩትን አይሁድ ሁሉ፥ በዚያም የተገኙትን ከለዳውያንን ሁሉ፤ ሰልፈኞች ሰዎችንም ሁሉ ገደላቸው።
ኤርምያስ 41:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስማኤል ማንም ሳያውቅ ጎዶልያስን ከገደለ በኋላ በሁለተኛው ቀን እንዲህ ሆነ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጎዶልያስ በተገደለ ማግስት፣ ማንም ስለ ሁኔታው ከማወቁ በፊት፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጎዶልያስ መገደል በኋላ ማንም ሳያውቅ በሁለተኛው ቀን አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱም ገዳልያ መሞቱን ማንም ሳያውቅ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጎዶልያስን ከገደለ በኋላ ማንም ሳያውቅ በሁለተኛው ቀን |
እስማኤልም ከጎዶልያስ ጋር በመሴፋ የነበሩትን አይሁድ ሁሉ፥ በዚያም የተገኙትን ከለዳውያንን ሁሉ፤ ሰልፈኞች ሰዎችንም ሁሉ ገደላቸው።
ጢማቸውን ላጭተው፥ ልብሳቸውንም ቀድደው እያለቀሱ ወደ እግዚአብሔር ቤት ያቀርቡ ዘንድ የእህል ቍርባንና ዕጣን በእጃቸው የያዙ፥ ሰማንያ ሰዎች ከሴኬምና ከሴሎ፥ ከሰማርያም መጡ።
ዳዊት እንዲህ አደረገ፤ በፍልስጥኤማውያንም ሀገር በሚቀመጥበት ዘመን ሁሉ ልማዱ ይህ ነበረ ብለው እንዳይናገሩብን ብሎ ዳዊት ወደ ጌት ያመጣቸው ዘንድ ወንድም ሆነ ሴትም ሆነ ማንንም በሕይወት አልተወም።