የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 38:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ይች ከተማ በባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ሠራ​ዊት እጅ በር​ግጥ ትሰ​ጣ​ለች፤ እር​ሱም ይይ​ዛ​ታል።”

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፤ ‘ይህች ከተማ በርግጥ ለባቢሎን ንጉሥ ሰራዊት ዐልፋ ትሰጣለች፤ እርሱም ይይዛታል።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ እንዲህ ይላልና፦ ይህች ከተማ በባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት እጅ በእርግጥ ትሰጣለች፥ እርሱም ይይዛታል።”

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንደገናም አስረዳቸው ዘንድ እግዚአብሔር የነገረኝ ቃል እንዲህ የሚል ነበር፦ “እኔ ይህችን ከተማ ለባቢሎናውያን ሠራዊት አሳልፌ እሰጣለሁ፤ እነርሱም በቊጥጥራቸው ሥር ያደርጉአታል።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ ይህች ከተማ በባቢሎን ንጉሥ ሠራዊት እጅ በእርግጥ ትሰጣለች፥ እርሱም ይይዛታል።

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 38:3
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለመ​ል​ካም ሳይ​ሆን ለክፉ ፊቴን በዚ​ህች ከተማ ላይ አድ​ር​ጌ​አ​ለ​ሁና፤ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ እጅ ትሰ​ጣ​ለች፤ እር​ሱም በእ​ሳት ያቃ​ጥ​ላ​ታል።”


የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ በቅ​ጥ​ርም ውጭ የከ​በ​ቡ​አ​ች​ሁን ከለ​ዳ​ው​ያ​ንን የም​ት​ወ​ጉ​በ​ትን በእ​ጃ​ችሁ ያለ​ውን የጦር መሣ​ሪ​ያ​ች​ሁን እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እነ​ዚ​ያ​ንም በዚ​ህች ከተማ መካ​ከል እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።


በዚ​ህች ከተማ ውስጥ የሚ​ቀ​መጥ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም ይሞ​ታል፤ ወጥቶ ወደ ከበ​ቡ​አ​ችሁ ወደ ከለ​ዳ​ው​ያን የሚ​ገባ ግን በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤ ሰው​ነ​ቱም ምርኮ ትሆ​ና​ለች።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዳ​ዊት ዙፋን ስለ ተቀ​መጠ ንጉሥ፥ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ስላ​ል​ተ​ማ​ረ​ኩት ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ፥ በዚ​ህች ከተማ ስለ​ሚ​ኖሩ ሕዝብ ሁሉ እን​ዲህ ይላ​ልና፦


ከለ​ዳ​ው​ያ​ንም ተመ​ል​ሰው ይህ​ችን ከተማ ይዋ​ጉ​አ​ታል፤ ይይ​ዙ​አ​ት​ማል፤ በእ​ሳ​ትም ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ታል።


ወደ ባቢ​ሎን ንጉሥ አለ​ቆች ባት​ወጣ ግን፥ ይች ከተማ በከ​ለ​ዳ​ው​ያን እጅ ትሰ​ጣ​ለች፤ በእ​ሳ​ትም ያቃ​ጥ​ሉ​አ​ታል፤ አን​ተም ከእ​ጃ​ቸው አታ​መ​ል​ጥም” አለው።