የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 34:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሰው ሁሉ ዕብ​ራዊ የሆነ ወንድ ባሪ​ያ​ው​ንና ዕብ​ራ​ዊት የሆ​ነች ሴት ባሪ​ያ​ውን አር​ነት እን​ዲ​ያ​ወጣ፥ አይ​ሁ​ዳዊ ወን​ድ​ሙ​ንም ማንም እን​ዳ​ይ​ገዛ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እያንዳንዱ ሰው፣ ዕብራዊ የሆነውን ወንድ ባሪያውንና ዕብራዊት የሆነችውን ሴት ባሪያውን ነጻ ማውጣት ነበረበት፤ ማንም ሰው አይሁዳዊ ወንድሙን በባርነት መግዛት አልነበረበትም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አዋጁም፦ ሰው ሁሉ ዕብራዊ የሆነውን ወንድ ባርያውንና ዕብራዊት የሆነችውን ሴት ባርያውን አርነት እንዲያወጣ፥ አይሁዳዊ ወንድሙንም ማንም እንዳይገዛ የሚል ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይኸውም ዕብራውያን ባሪያዎቻቸውን በሙሉ ሴቶችንም ወንዶችንም ነጻ ለማውጣት ነበር፤ ማንም ሰው እስራኤላውያን ከሆኑት ወገኖቹ መካከል ባሪያ እንዳይኖረው ወሰኑ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 34:9
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከአ​መ​ለ​ጡ​ትም አንድ ሰው መጣ፤ ለዕ​ብ​ራ​ዊው ለአ​ብ​ራ​ምም ነገ​ረው፤ እር​ሱም የኤ​ስ​ኮል ወን​ድ​ምና የአ​ው​ናን ወን​ድም በሆነ በአ​ሞ​ራ​ዊው የመ​ምሬ ዛፍ ይኖር ነበር፤ እነ​ዚ​ያም ከአ​ብ​ራም ጋር ቃል ኪዳን ገብ​ተው ነበር።


ሌቦች በስ​ውር ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ሀገር ሰር​ቀ​ው​ኛ​ልና፤ በዚ​ህም ደግሞ ምንም ያደ​ረ​ግ​ሁት ሳይ​ኖር በግ​ዞት ቤት አኑ​ረ​ው​ኛ​ልና።”


ሣጥ​ኑን በከ​ፈ​ተ​ችም ጊዜ ሕፃ​ኑን አየች፤ እነ​ሆም፥ ሕፃኑ በሣ​ጥኑ ውስጥ ያለ​ቅስ ነበር፤ የፈ​ር​ዖ​ንም ልጅ አዘ​ነ​ች​ለት፥ “ይህ ሕፃን ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ልጆች አንዱ ነው” አለች።


እነ​ር​ሱም ቃል​ህን ይሰ​ማሉ፤ አን​ተና የእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ወደ ግብፅ ንጉሥ ትገ​ባ​ላ​ችሁ፦ የዕ​ብ​ራ​ው​ያን አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጠር​ቶ​ናል፤ አሁ​ንም ለአ​ም​ላ​ካ​ችን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ሠዋ ዘንድ የሦ​ስት ቀን መን​ገድ ወደ ምድረ በዳ እን​ሄ​ዳ​ለን ትሉ​ታ​ላ​ችሁ።


ብዙ አሕ​ዛ​ብና ታላ​ላ​ቆች ነገ​ሥ​ታት እነ​ር​ሱን ይገ​ዙ​አ​ቸ​ዋል፤ እኔም እንደ አደ​ራ​ረ​ጋ​ቸ​ውና እንደ እጃ​ቸው ሥራ እከ​ፍ​ላ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


የገዛ ራሱም ምድር ጊዜ እስ​ኪ​መጣ ድረስ አሕ​ዛብ ሁሉ ለእ​ር​ሱና ለልጁ ለልጅ ልጁም ይገ​ዛሉ፤ በዚ​ያን ጊዜም ብዙ አሕ​ዛ​ብና ታላ​ላ​ቆች ነገ​ሥ​ታት ለእ​ርሱ ይገ​ዙ​ለ​ታል።


በዚያ ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ቀን​በ​ርን ከአ​ን​ገ​ትህ እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ እስ​ራ​ት​ህ​ንም እበ​ጥ​ሳ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ለሌላ አት​ገ​ዛም።


ሰው ሁሉ ወንድ ባሪ​ያ​ው​ንና ሴት ባሪ​ያ​ውን አር​ነት እን​ዲ​ያ​ወጣ፥ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም ማንም እን​ዳ​ይ​ገ​ዛ​ቸው ወደ ቃል ኪዳኑ የገቡ አለ​ቆች ሁሉና ሕዝቡ ሁሉ ሰሙ፤ አር​ነ​ትም አወ​ጡ​አ​ቸው።


አሁ​ንም ቢሆን፥ እና​ንተ ዐመ​ፀ​ኞ​ችና ቀማ​ኞች ናችሁ፤ እን​ደ​ዚ​ህም ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን ትበ​ድ​ላ​ላ​ችሁ።


እነ​ርሱ ዕብ​ራ​ው​ያን ቢሆኑ እኔም እንደ እነ​ርሱ ነኝ፤ እነ​ርሱ እስ​ራ​ኤ​ላ​ው​ያን ቢሆኑ እኔም እንደ እነ​ርሱ ነኝ፤ እነ​ርሱ የአ​ብ​ር​ሃም ልጆች ቢሆኑ እኔም እንደ እነ​ርሱ ነኝ።


“አን​ተም ወን​ድ​ም​ህን ዕብ​ራ​ዊ​ዉን ወይም ዕብ​ራ​ዊ​ቱን ብት​ገዛ ስድ​ስት ዓመት ያገ​ል​ግ​ሉህ፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ዓመት ከአ​ንተ ዘንድ አር​ነት አው​ጥ​ተህ ልቀ​ቀው።


በስ​ም​ን​ተ​ኛው ቀን የተ​ገ​ዘ​ርሁ፥ ከእ​ስ​ራ​ኤል ሕዝብ ከብ​ን​ያም ነገድ ከዕ​ብ​ራ​ው​ያን ዕብ​ራዊ ነኝ፤ በኦ​ሪ​ትም ፈሪ​ሳዊ ነበ​ርሁ።


ሁለ​ታ​ቸ​ውም ወደ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሰፈር ገቡ፤ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም “እነሆ፥ ዕብ​ራ​ው​ያን ከተ​ሸ​ሸ​ጉ​በት ጕድ​ጓድ ይወ​ጣሉ” አሉ።


ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም የእ​ል​ል​ታ​ውን ድምፅ በሰሙ ጊዜ፥ “በዕ​ብ​ራ​ው​ያን ሰፈር ያለው ይህ ታላቅ የእ​ል​ልታ ድምፅ ምን​ድን ነው?” አሉ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት ወደ ሰፈሩ እንደ ደረ​ሰች አስ​ተ​ዋሉ።


እና​ንተ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ሆይ! በርቱ፤ ጐብዙ፤ እና​ንተ ባሪ​ያ​ዎች እን​ዳ​ደ​ረ​ጋ​ች​ኋ​ቸው ዕብ​ራ​ው​ያን ባሪ​ያ​ዎች እን​ዳ​ያ​ደ​ር​ጓ​ችሁ በርቱ፤ ተዋጉ።”