የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 30:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለአ​ም​ላ​ካ​ቸው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ ለማ​ስ​ነ​ሣ​ላ​ቸው ለን​ጉ​ሣ​ቸው ለዳ​ዊ​ትም ይገ​ዛሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን ለአምላካቸው ለእግዚአብሔር፣ ለማስነሣላቸውም ለንጉሣቸው፣ ለዳዊት ይገዛሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን ጌታ አምላካቸውንና የማስነሣላቸውን ንጉሣቸውን ዳዊትን ያገለግላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህ ፈንታ ለእኔ ለአምላካቸው ይሰግዱልኛል፤ እኔ በዙፋን ላይ ለማስቀምጥላቸው የዳዊት ዘር ለሆነውም ንጉሣቸው ይገዛሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለአምላካቸው ለእግዚአብሔርም ለማስነሣላቸው ለንጉሣቸው ለዳዊትም ይገዛሉ እንጂ ሌሎች አሕዛብ እንደ ገና አይገዙአቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 30:9
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እነሆ ለዳ​ዊት የጽ​ድቅ ቍጥ​ቋጥ የማ​ስ​ነ​ሣ​በት ዘመን ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ንጉሥ ይነ​ግ​ሣል፤ ያስ​ባል፤ በም​ድ​ርም ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን ያደ​ር​ጋል።


ለእ​ና​ንተ የማ​ስ​ባ​ትን አሳብ እኔ አው​ቃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ፍጻ​ሜና ተስፋ እሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ የሰ​ላም አሳብ ነው እንጂ የክፉ ነገር አይ​ደ​ለም።


አለ​ቃ​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ ውስጥ ይሾ​ማል፤ ገዢ​አ​ቸ​ውም ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው ይወ​ጣል፤ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ እኔም እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ወደ እኔ ይመ​ለስ ዘንድ ልብ የሰ​ጠው ማን ነው? ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


በዚ​ያም ዘመን በዚ​ያም ጊዜ ለዳ​ዊት የጽ​ድ​ቅን ቍጥ​ቋጥ አበ​ቅ​ል​ለ​ታ​ለሁ፤ እር​ሱም ፍር​ድ​ንና ጽድ​ቅን በም​ድር ያደ​ር​ጋል።


ከዚ​ያም በኋላ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ተመ​ል​ሰው አም​ላ​ካ​ቸ​ውን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ንጉ​ሣ​ቸ​ውን ዳዊ​ትን ይፈ​ል​ጋሉ፤ በኋ​ለ​ኛ​ውም ዘመን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ቸር​ነ​ቱን ያስ​ቡ​ታል።


ከባ​ር​ያው ከዳ​ዊት ቤት የም​ን​ድ​ን​በ​ትን ቀንድ አስ​ነ​ሣ​ልን፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተስፋ እንደ ሰጣ​ቸው ከዳ​ዊት ዘር ለእ​ስ​ራ​ኤል መድ​ኀ​ኒት አድ​ርጎ ኢየ​ሱ​ስን አመ​ጣ​ላ​ቸው።


መፍ​ረስ መበ​ስ​በ​ስ​ንም እን​ዳ​ያይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሙ​ታን ለይቶ እን​ዳ​ስ​ነ​ሣው እን​ዲህ አለ፦ ‘የታ​መ​ነ​ውን የዳ​ዊ​ትን ቅዱስ ተስፋ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ።


ነቢይ ስለ ነበረ፥ ከአ​ብ​ራ​ኩም የተ​ገ​ኘ​ውን በዙ​ፋኑ እን​ዲ​ያ​ነ​ግ​ሥ​ለት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሐ​ላን እንደ ማለ​ለት ስለ ዐወቀ፥