የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 28:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከጥ​ንት ከእ​ኔና ከአ​ንተ በፊት የነ​በሩ ነቢ​ያት በብዙ ሀገ​ርና በታ​ላ​ላቅ መን​ግ​ሥ​ታት ላይ ስለ ሰል​ፍና ስለ ክፉ ነገር ስለ ቸነ​ፈ​ርም ትን​ቢት ተና​ገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከአንተና ከእኔ በፊት ጥንት የተነሡ ነቢያት፣ በብዙ አገሮችና በታላላቅ መንግሥታት ላይ ስለ ጦርነት፣ ስለ ጥፋትና ስለ መቅሠፍት ትንቢት ተናግረዋል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከጥንት ከእኔና ከአንተ በፊት የነበሩ ነቢያት በብዙ አገርና በታላላቅ መንግሥታት ላይ ስለ ጦርነትና ስለ ክፉ ነገር ስለ ቸነፈርም ትንቢት ተናገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በጥንት ዘመን ከእኔና ከአንተ በፊት የተነሡ ነቢያት በብዙ ሕዝብና በታላላቅ መንግሥታት ላይ ጦርነት፥ ራብና ቸነፈር እንደሚመጣ ትንቢት ተናግረዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከጥንት ከእኔና ከአንተ በፊት የነበሩ ነቢያት በብዙ አገርና በታላላቅ መንግሥታት ላይ ስለ ሰልፍና ስለ ክፉ ነገር ስለ ቸነፈርም ትንቢት ተናገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 28:8
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በገ​ለ​ዓድ ቴስ​ባን የነ​በ​ረው ቴስ​ብ​ያ​ዊው ነቢዩ ኤል​ያስ አክ​ዓ​ብን፥ “በፊቱ የቆ​ም​ሁት የኀ​ያ​ላን አም​ላክ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ከአፌ ቃል በቀር በእ​ነ​ዚህ ዓመ​ታት ዝና​ብም ጠልም አይ​ወ​ር​ድም” አለው።


እር​ሱም አለ፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እስ​ራ​ኤል ሁሉ ጠባቂ እን​ደ​ሌ​ላ​ቸው በጎች በተ​ራ​ሮች ላይ ተበ​ት​ነው አየሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ነ​ዚህ አም​ላክ አይ​ደ​ለ​ምን? እያ​ን​ዳ​ንዱ በሰ​ላም ወደ ቤቱ ይመ​ለስ።”


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ን​ጠ​ይ​ቅ​በት የይ​ምላ ልጅ ሚክ​ያስ የሚ​ባል አንድ ሰው አለ፤ ነገር ግን ክፉ እንጂ መል​ካም አይ​ና​ገ​ር​ል​ኝ​ምና እጠ​ላ​ዋ​ለሁ” አለው። የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም፥ “ንጉሥ እን​ዲህ አይ​በል” አለ።


የአ​ሞጽ ልጅ ኢሳ​ይ​ያስ በባ​ቢ​ሎን ላይ ያየው ራእይ።


ፍላ​ጾ​ቻ​ቸ​ውም ጐበ​ዞ​ችን ይጨ​ፈ​ጭ​ፋሉ፤ ሕፃ​ኖ​ቻ​ች​ሁ​ንም አይ​ም​ሩም፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ለል​ጆ​ቻ​ችሁ አይ​ራ​ሩም።


በቴ​ቁሔ በላም ጠባ​ቂ​ዎች መካ​ከል የነ​በረ አሞጽ በይ​ሁዳ ንጉሥ በዖ​ዝ​ያን ዘመን፥ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ በዮ​አስ ልጅ በኢ​ዮ​ር​ብ​ዓም ዘመን፥ የም​ድር መና​ወጥ ከሆ​ነ​በት ከሁ​ለት ዓመት በፊት ስለ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ያየው ቃል ይህ ነው።


እን​ዲ​ህም አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጽ​ዮን ሆኖ ድም​ፁን ከፍ አድ​ርጎ ይና​ገ​ራል፤ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ሆኖ ቃሉን ይሰ​ጣል፤ የእ​ረ​ኞ​ችም ማሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎች ያለ​ቅ​ሳሉ፤ የቀ​ር​ሜ​ሎ​ስም ራስ ይደ​ር​ቃል።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል ሁለ​ተኛ ወደ ዮናስ እን​ዲህ ሲል መጣ፦