የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 27:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰን​ሰ​ለ​ትና ቀን​በር ሥራ፤ በአ​ን​ገ​ት​ህም ላይ አድ​ርግ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፤ “የዕንጨት ቀንበር ሠርተህ በጠፍር ማነቆ አያይዘውና በዐንገትህ አስገባው፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ እንዲህ አለኝ፦ ጠፍርንና ቀንበርን ሥራ በአንገትህም ላይ አድርግ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“የጠፍር ማሰሪያና ማነቆ ያለው ቀንበር ከእንጨት ሠርተህ በጫንቃህ ላይ ተሸከም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔር እንዲህ ይለኛል፦ እስራትና ቀንበር ሥራ በአንገትህም ላይ አድርግ፥

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 27:2
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የከ​ሓና ልጅ ሴዴ​ቅ​ያ​ስም የብ​ረት ቀን​ዶች ሠርቶ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በእ​ነ​ዚህ ቀን​ዶች ሶር​ያ​ው​ያ​ንን ትወ​ጋ​ቸ​ዋ​ለህ” አለ።


ኤዶ​ም​ያ​ስ​ንም፥ ሞዓ​ብ​ንም፥ የአ​ሞ​ን​ንም ልጆች፤


ነገር ግን ከባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ቀን​በር በታች አን​ገ​ቱን ዝቅ የሚ​ያ​ደ​ር​ገ​ው​ንና የሚ​ገ​ዛ​ለ​ትን ሕዝብ በሀ​ገሩ ላይ እተ​ወ​ዋ​ለሁ፤ እር​ሱም ያር​ሳ​ታል፤ ይቀ​መ​ጥ​ባ​ት​ማል።”


ለይ​ሁዳ ንጉሥ ለሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስም ይህን ቃል ሁሉ ተና​ገ​ርሁ፥ “ከባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ቀን​በር በታች አን​ገ​ታ​ች​ሁን ዝቅ አድ​ርጉ፤ ለእ​ር​ሱና ለሕ​ዝ​ቡም ተገ​ዙ​ላ​ቸው በሕ​ይ​ወ​ትም ኑሩ።


በዚያ ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፥ ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ቀን​በ​ርን ከአ​ን​ገ​ትህ እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ እስ​ራ​ት​ህ​ንም እበ​ጥ​ሳ​ለሁ፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ ለሌላ አት​ገ​ዛም።


የግ​ብ​ፅን ቀን​በር በዚያ በሰ​በ​ርሁ ጊዜ በጣ​ፍ​ናስ ቀኑ ይጨ​ል​ማል፤ የኀ​ይ​ል​ዋም ትዕ​ቢት ይጠ​ፋ​ባ​ታል፤ ደመ​ናም ይጋ​ር​ዳ​ታል፤ ሴቶች ልጆ​ች​ዋም ይማ​ረ​ካሉ።


“ምድር በአ​ሕ​ዛብ እንደ ተመ​ላች፥ ከተ​ማም በኀ​ጢ​አት ተመ​ል​ታ​ለ​ችና ሰን​ሰ​ለት ሥራ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም ከም​ሥ​ራቅ አን​በጣ ይመ​ጣል፤ አን​ዱም ኵብ​ኵባ ንጉሡ ጎግ ነበረ።


ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እን​ዲህ አሳ​የኝ፤ እነ​ሆም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመ​ፍ​ረድ በቃሉ እሳ​ትን ጠራ፤ እር​ስ​ዋም ታላ​ቁን ቀላ​ይና ምድ​ርን በላች።