የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 23:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስለ​ዚህ እነሆ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሕዝብ ከግ​ብፅ ምድር ያወጣ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ዳግ​መኛ የማ​ይ​ባ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ስለዚህ ሰዎች፣ ‘እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን!’ ብለው ከእንግዲህ የማይምሉበት ዘመን ይመጣል ይላል እግዚአብሔር፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“ስለዚህ፥ እነሆ፦ ‘የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ያወጣ በሕያው ጌታ እምላለሁ!’ ብለው ዳግመኛ የማይምሉበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፤

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ሰዎች ‘የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው የማይምሉበት ጊዜ ይመጣል።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለዚህ፥ እነሆ፦ የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን! ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 23:7
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚ​ያም ቀን እን​ዲህ ይሆ​ናል፤ ከአ​ሦ​ርና ከግ​ብፅ፥ ከባ​ቢ​ሎ​ንና ከኢ​ት​ዮ​ጵያ፥ ከኤ​ላ​ሜ​ጤን፥ ከም​ሥ​ራ​ቅና ከም​ዕ​ራብ ለቀ​ሩት ለሕ​ዝቡ ቅሬታ ይቀና ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገና እጁን ይገ​ል​ጣል።


እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፤ ዘር​ህ​ንም ከም​ሥ​ራቅ አመ​ጣ​ዋ​ለሁ፤ ከም​ዕ​ራ​ብም እሰ​በ​ስ​ብ​ሃ​ለሁ።


የሕ​ዝ​ቤን ቅሬታ ከበ​ተ​ን​ኋ​ቸው ምድር ሁሉ ወደ መሰ​ማ​ሪ​ያ​ቸው ሰብ​ስቤ እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይበ​ዛሉ፤ ይባ​ዛ​ሉም።


እነሆ! የሕ​ዝ​ቤን የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንና የይ​ሁ​ዳን ምርኮ የም​መ​ል​ስ​በት ዘመን ይመ​ጣ​ልና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ወደ ሰጠ​ኋት ምድር እመ​ል​ሳ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይገ​ዙ​አ​ታል።”


ብሬ​ንና ወር​ቄን ወስ​ዳ​ች​ኋ​ልና፥ የተ​ወ​ደ​ደ​ው​ንም መል​ካ​ሙን ዕቃ​ዬን ወደ ቤተ መቅ​ደ​ሳ​ችሁ አግ​ብ​ታ​ች​ኋ​ልና፥


ከግብጽ ምድር እንደ ወጣህበት ዘመን ተአምራትን አሳያቸዋለሁ።