የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ኤርምያስ 16:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዚህ ስፍራ ስለ ተወ​ለዱ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆች፥ ስለ ወለ​ዱ​አ​ቸ​ውም ስለ እና​ቶ​ቻ​ቸው፥ በዚ​ህ​ችም ምድር ስለ ወለ​ዱ​አ​ቸው ስለ አባ​ቶ​ቻ​ቸው እን​ዲህ ይላ​ልና፦

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህች ምድር ስለሚወለዱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች፣ እንዲሁም ስለ እናቶቻቸው ስለ አባቶቻቸው እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ በዚህ ስፍራ በተወለዱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች፥ በወለዱአቸውም እናቶቻቸው፥ በዚህችም ምድር በወለዱአቸው አባቶቻቸው ላይ እንዲህ ይላልና፦

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚህ ስፍራ በሚወለዱ ልጆችና እነርሱንም በሚወልዱአቸው ወላጆች ላይ የሚደርስባቸውን እነግርሃለሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔር በዚህ ስፍራ ስለ ተወለዱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች፥ ስለወለዱአቸውም ስለ እናቶቻቸው፥ በዚህችም ምድር ስለ ወለዱአቸው ስለ አባቶቻቸው እንዲህ ይላልና፦

ምዕራፉን ተመልከት



ኤርምያስ 16:3
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መበ​ለ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ከባ​ሕር አሸዋ ይልቅ በዝ​ተ​ዋል፤ በብ​ላ​ቴ​ኖች እናት ላይ በቀ​ትር ጊዜ አጥ​ፊ​ውን አም​ጥ​ቻ​ለሁ፤ ጭን​ቀ​ት​ንና ድን​ጋ​ጤን በድ​ን​ገት አም​ጥ​ቼ​ባ​ታ​ለሁ።


በዚህ ስፍራ ሚስት አታ​ግባ፥ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ንም አት​ው​ለድ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰላ​ሜን፥ ቸር​ነ​ቴ​ንና ምሕ​ረ​ቴን፥ ከዚህ ሕዝብ አስ​ወ​ግ​ጄ​አ​ለ​ሁና ልቅሶ ወዳ​ለ​በት ቤት አት​ግባ፤ ታለ​ቅ​ስና ታዝ​ንም ዘንድ አት​ሂድ።


ስለ​ዚ​ህም የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት በዘ​መ​ና​ች​ሁም የእ​ል​ል​ታን ድም​ፅና የደ​ስ​ታን ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽ​ራን ድም​ፅና የሴት ሙሽ​ራን ድምፅ ከዚህ ስፍራ አስ​ቀ​ራ​ለሁ።


ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ በዚህ ሕዝብ ላይ ደዌን አሳ​ድ​ራ​ለሁ፤ አባ​ቶ​ችና ልጆ​ችም በአ​ን​ድ​ነት ይታ​መ​ማሉ፤ ጎረ​ቤ​ትና ባል​ን​ጀ​ራም ይጠ​ፋሉ።


ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ተና​ገር፤ እን​ዲ​ህም በል፦ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የኀ​ይ​ላ​ች​ሁን ትም​ክ​ሕት፥ የዐ​ይ​ና​ች​ሁን አም​ሮት፥ የነ​ፍ​ሳ​ች​ሁ​ንም ምኞት፥ መቅ​ደ​ሴን አረ​ክ​ሳ​ለሁ፤ ያስ​ቀ​ራ​ች​ኋ​ቸ​ውም ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ቻ​ችሁ በሰ​ይፍ ይወ​ድ​ቃሉ።