ሆሴዕ 5:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚያድኑ አዳኞች ያጠምዱባት ዘንድ ተከሏት፤ እኔ ግን መካሪያችሁ ነኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐመፀኞች በግድያ በርትተዋል፤ ሁሉንም እቀጣቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓመፀኞችም እርድ አብዝተዋል፤ እኔ ግን እነርሱን ሁሉ እገሥጻለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዐመፀኞች የግድያ ሥራቸውን አስፋፍተዋል፤ ስለዚህ ሁሉንም እቀጣቸዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓመፀኞችም እርድ አብዝተዋል፥ እኔ ግን እነዚያን ሁሉ እዘልፋለሁ። |
ምክራቸውን ጥልቅ አድርገው ከእግዚአብሔር ለሚሰውሩ ወዮላቸው! ሥራቸውንም በጨለማ ውስጥ አድርገው፥ “ማን ያየናል? ወይስ ማን ያውቀናል?” ለሚሉ ወዮላቸው!
እነርሱም፥ “ሕግ ከካህን፥ ምክርም ከጠቢብ፥ ቃልም ከነቢይ አይጠፋምና ኑ፤ በኤርምያስ ላይ ምክርን እንምከር። ኑ፤ በምላስ እንምታው፤ ቃሉንም ሁሉ አናዳምጥ” አሉ።
አቤቱ! ዐይኖችህ ለሃይማኖት አይደሉምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል፤ ነገር ግን አላዘኑም፤ ቀጥቅጠሃቸውማል፤ ነገር ግን ተግሣጽን እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ይመለሱም ዘንድ እንቢ አሉ።
ክፋታቸውም ሁሉ በጌልገላ አለ፤ በዚያ ጠልቻቸዋለሁ፤ ስለ ሠሩት ክፋት ከቤቴ አሳድዳቸዋለሁ፤ ከእንግዲህ ወዲያ አልወድዳቸውም፤ አለቆቻቸው ሁሉ ዐመፀኞች ናቸውና።