የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ሆሴዕ 4:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ነገር ግን ሕዝቤ እን​ደ​ሚ​ከ​ራ​ከር ካህን ነውና እን​ግ​ዲህ የሚ​ከ​ራ​ከር፥ ማንም አይ​ኑር፥ የሚ​ዘ​ል​ፍም ማንም አይ​ኑር።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ነገር ግን ማንም ሰው አይከራከር፤ ማንም ሌላውን አይወንጅል፤ በካህናት ላይ ክስን እንደሚያቀርቡ፣ ሕዝብህ እንደዚያው ናቸውና።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን ሙግቴ ከካህን ጋር ነውና ማንም አይከራከር፥ ማንም አይዝለፍ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ የምወቅሰው እናንተን ካህናትን ስለ ሆነ ሕዝቡን የሚከስ ወይም የሚወቀስ አይኑር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን ሕዝብህ ከካህን ጋር እንደሚከራከሩ ናቸውና ማንም አይከራከር፥ ማንም አይዝለፍ።

ምዕራፉን ተመልከት



ሆሴዕ 4:4
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነ​ር​ሱም፥ “ሕግ ከካ​ህን፥ ምክ​ርም ከጠ​ቢብ፥ ቃልም ከነ​ቢይ አይ​ጠ​ፋ​ምና ኑ፤ በኤ​ር​ም​ያስ ላይ ምክ​ርን እን​ም​ከር። ኑ፤ በም​ላስ እን​ም​ታው፤ ቃሉ​ንም ሁሉ አና​ዳ​ምጥ” አሉ።


እኔም ምላ​ስ​ህን ከት​ና​ጋህ ጋር አጣ​ብ​ቃ​ታ​ለሁ፤ አን​ተም ዲዳ ትሆ​ና​ለህ፤ እነ​ር​ሱም ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና የሚ​ዘ​ልፍ ሰው አት​ሆ​ን​ባ​ቸ​ውም።


እን​ዲ​ሁም ኤፍ​ሬም ከጣ​ዖ​ታት ጋር ተጋ​ጠመ፤ ለራ​ሱም ዕን​ቅ​ፋ​ትን አኖረ።


በበሩ የሚ​ገ​ሥ​ጸ​ውን ጠሉ፤ እው​ነ​ት​ንም የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ተጸ​የፉ።


ስለ​ዚህ ዘመኑ ክፉ ነውና በዚያ ዘመን አስ​ተ​ዋይ ዝም ይላል።


አጥ​ን​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ከቤት ያወጡ ዘንድ ቤተ​ሰ​ቦ​ቻ​ቸው በወ​ሰ​ዱ​አ​ቸው ጊዜ፥ ቤት ጠባ​ቂ​ውን በአ​ንተ ዘንድ የቀረ አለን? በአ​ለው ጊዜ እርሱ የለም ይላል። ያም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ስም እን​ዳ​ት​ጠራ ዝም በል ይለ​ዋል።


ማና​ቸ​ውም ሰው ቢኰራ፥ በአ​ም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ለማ​ገ​ል​ገል የሚ​ቆ​መ​ውን ካህ​ኑን ወይም በዚያ ወራት ያለ​ውን ፈራ​ጁን ባይ​ሰማ ያ ሰው ይሙት፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ዘንድ ክፉ​ውን አስ​ወ​ግዱ፤