የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 46:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እኔ ወደ ግብፅ አብ​ሬህ እወ​ር​ዳ​ለሁ፤ ከዚ​ያም ደግሞ እኔ አወ​ጣ​ሃ​ለሁ፤ ልጅህ ዮሴ​ፍም እጁን በዐ​ይ​ንህ ላይ ያኖ​ራል።”

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ዐብሬህ ወደ ግብጽ እወርዳለሁ፤ ከዚያም መልሼ አወጣሃለሁ፤ የዮሴፍ የራሱ እጆችም ዐይኖችህን ይገጥሟቸዋል።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔ ወደ ግብጽ አብሬህ እወርዳለሁ፥ ከዚያም ደግሞ እኔ አወጣሃለሁ፥ የዮሴፍም እጅ ዓይንህን ይሸፍናል።”

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እኔ ወደ ግብጽ አብሬህ እሄዳለሁ፤ ወደዚህ ምድርም ትውልድህን መልሼ አመጣለሁ፤ በምትሞትበትም ጊዜ ዮሴፍ በአጠገብህ ይገኛል።”

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔ ወደ ግብፅ አብሬህ እወርዳለሁ ከዚያንም ደግሞ እኔ አወጣሃለሁ፤ ዮሴፍም እጁን በዓይንህ ላይ ያኖራል።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 46:4
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነ​ሆም፥ እኔ ከአ​ንተ ጋር እሄ​ዳ​ለሁ፤ በም​ት​ሄ​ድ​በ​ትም መን​ገድ ሁሉ እጠ​ብ​ቅ​ሃ​ለሁ፤ ወደ​ዚ​ያ​ችም ምድር እመ​ል​ስ​ሃ​ለሁ፤ የነ​ገ​ር​ሁ​ህን ሁሉ እስ​ካ​ደ​ር​ግ​ልህ ድረስ አል​ተ​ው​ህ​ምና።”


እስ​ራ​ኤ​ልም ዮሴ​ፍን፥ “እነሆ፥ እኔ እሞ​ታ​ለሁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ከእ​ና​ንተ ጋር ይሆ​ናል፤ ወደ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም ምድር ይመ​ል​ሳ​ች​ኋል፤


ዮሴ​ፍም በአ​ባቱ ፊት ወደቀ፤ በእ​ር​ሱም ላይ አለ​ቀሰ፤ ሳመ​ውም።


ልጆ​ቹም ወደ ከነ​ዓን ምድር መለ​ሱት፤ ባለ ሁለት ክፍል በሆ​ነች ዋሻም ቀበ​ሩት፤ እር​ስ​ዋም በመ​ምሬ ፊት ያለች፥ አብ​ር​ሃም ለመ​ቃ​ብር ርስት ከኬ​ጢ​ያ​ዊው ከኤ​ፍ​ሮን ከእ​ር​ሻው ጋር የገ​ዛት ዋሻ ናት።


አባቴ ሳይ​ሞት አም​ሎ​ኛል፤ እን​ዲህ ሲል፦ ‘እነሆ እኔ እሞ​ታ​ለሁ፤ በቈ​ፈ​ር​ሁት መቃ​ብር በከ​ነ​ዓን ምድር በዚያ ቅበ​ረኝ።’ አሁ​ንም ወጥቼ አባ​ቴን ልቅ​በ​ርና ልመ​ለስ።”


እን​ዲ​ህም አልሁ፦ ከግ​ብፅ መከራ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያን፥ ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያን፥ ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያን ሀገር፥ ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስስ ሀገር አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤


ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም እጅ አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ ከዚ​ያ​ችም ሀገር ወተ​ትና ማር ወደ​ም​ታ​ፈ​ስ​ሰው ሀገር፥ ወደ ሰፊ​ዪ​ቱና ወደ መል​ካ​ሚቱ ሀገር፥ ወደ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኬጤ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም፥ ወደ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ው​ያ​ንም ስፍራ አወ​ጣ​ቸው ዘንድ ወረ​ድሁ።