የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 42:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የዮ​ሴ​ፍን ወን​ድም ብን​ያ​ምን ግን ያዕ​ቆብ ከወ​ን​ድ​ሞቹ ጋር አል​ሰ​ደ​ደ​ውም፥ “ምና​ል​ባት ክፉ እን​ዳ​ያ​ገ​ኘው” ብሎ​አ​ልና።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን ያዕቆብ የዮሴፍን ወንድም ብንያምን፣ ክፉ ነገር ይደርስበታል በሚል ፍርሀት ከወንድሞቹ ጋራ አልላከውም።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን ያዕቆብ የዮሴፍን ወንድም ብንያምን፥ ክፉ ነገር ይደርስበታል በሚል ፍርሀት ከወንድሞቹ ጋር አላከውም።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ነገር ግን “ጒዳት ይደርስበታል” ብሎ ስለ ፈራ ያዕቆብ ከዮሴፍ ጋር ከአንድ እናት የወለደውን ልጁን ብንያምን ከወንድሞቹ ጋር ወደ ግብጽ አላከውም፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የዮሴፍ ወንድም ብንያምን ግን ያዕቆብ ከወንድሞቹ ጋር አልሰደደውም፦ ምናልባት ክፋ እንዳያግኘው ብሎአልና።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 42:4
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርስ በር​ሳ​ቸ​ውም፥ “ኑ ለእኛ ከተ​ማና ራሱ ወደ ሰማይ የሚ​ደ​ርስ ግንብ እን​ሥራ፤ በም​ድር ፊት ሁሉ ላይ ሳን​በ​ተን ስማ​ች​ንን እና​ስ​ጠ​ራው” ተባ​ባሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም አለ፥ “እነሆ፥ አዳም መል​ካ​ም​ንና ክፉን ለማ​ወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ አሁ​ንም እጁን እን​ዳ​ይ​ዘ​ረጋ፥ ደግ​ሞም ከሕ​ይ​ወት ዛፍ ወስዶ እን​ዳ​ይ​በላ፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ሕያው ሆኖ እን​ዳ​ይ​ኖር፥”


የራ​ሔል ልጆች፤ ዮሴፍ፥ ብን​ያም፤


የዮ​ሴ​ፍም ዐሥሩ ወን​ድ​ሞቹ እህ​ልን ከግ​ብፅ ይሸ​ምቱ ዘንድ ወረዱ፤


እር​ሱም አለ፥ “ልጄ ከእ​ና​ንተ ጋር አይ​ወ​ር​ድም፤ ወን​ድሙ ሞቶ እርሱ ብቻ ቀር​ቶ​አ​ልና፤ በም​ት​ሄ​ዱ​በት መን​ገድ ምና​ል​ባት ክፉ ነገር ቢያ​ገ​ኘው ሽም​ግ​ል​ና​ዬን በኀ​ዘን ወደ መቃ​ብር ታወ​ር​ዱ​ታ​ላ​ችሁ።”


አም​ላ​ኬም በዚያ ሰው ፊት ሞገ​ስን ይስ​ጣ​ችሁ፤ ያን ወን​ድ​ማ​ች​ሁ​ንና ብን​ያ​ም​ንም ይመ​ል​ስ​ላ​ችሁ፤ እኔም ልጆ​ችን እን​ዳ​ጣሁ አጣሁ።”


ዮሴ​ፍም ዐይ​ኑን አን​ሥቶ የእ​ና​ቱን ልጅ ወን​ድሙ ብን​ያ​ምን አየው፤ እር​ሱም አለ፥ “ወደ አንተ እና​መ​ጣ​ዋ​ለን ብላ​ችሁ የነ​ገ​ራ​ች​ሁኝ ታናሽ ወን​ድ​ማ​ችሁ ይህ ነውን?” እነ​ር​ሱም፥ “አዎን” አሉት። እን​ዲ​ህም አለው፥ “ልጄ ሆይ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅር ይበ​ልህ።”