የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 40:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሁለ​ቱም በአ​ን​ዲት ሌሊት ሕል​ምን አለሙ። በግ​ዞት ቤት የነ​በ​ሩት የግ​ብፅ ንጉሥ ጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎች አለ​ቃና የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎች አለቃ ሁለ​ቱም እየ​ራ​ሳ​ቸው ሕል​ምን አለሙ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ታስረው የነበሩት የግብጽ የንጉሥ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ ቤቱ አዛዥ፣ በአንድ ሌሊት የየራሳቸውን ሕልም አዩ፤ የሁለቱም ሕልም ለየራሱ የተለየ ፍች ነበረው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ታስረው የነበሩት የግብጽ የንጉሥ የመጠጥ አሳላፊዎች አለቃና የእንጀራ ቤቱ አዛዥ፥ በአንድ ሌሊት የየራሳቸውን ሕልም አዩ፤ የሁለቱም ሕልም ለየራሱ የተለየ ፍቺ ነበረው።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የንጉሡ የወይን ጠጅ አሳላፊና የእንጀራ ቤት ኀላፊ ሁለቱም በእስር ቤት ሳሉ በአንድ ሌሊት ሕልም አዩ፤ የእያንዳንዳቸው ሕልም የተለያየ ትርጒም ነበረው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በግዞት ቤት የነበሩት የግብፅ ንጉሥ ጠጅ አሳላፊና እንጀራ አበዛ ሁለቱም በአንዲት ሌሊት እንደ ሕልሙ ትርጓሜ እየራሳቸው ሕልምን አለሙ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 40:5
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚ​ያች ሌሊ​ትም አቤ​ሜ​ሌክ ተኝቶ ሳለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሕ​ልም ወደ እርሱ መጣ፤ እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ አንተ ስለ ወሰ​ድ​ሃት ሴት ትሞ​ታ​ለህ፤ እር​ስዋ ባለ ባል ናትና።”


ከዚህ ነገር በኋ​ላም እን​ዲህ ሆነ፤ የግ​ብፅ ንጉሥ የጠጅ አሳ​ላ​ፊ​ዎች አለ​ቃና የእ​ን​ጀራ አበ​ዛ​ዎች አለቃ ጌታ​ቸ​ውን የግ​ብፅ ንጉ​ሥን በደሉ።


የእ​ስር ቤቱ ዘበ​ኞች አለ​ቃም ለዮ​ሴፍ አሳ​ልፎ ሰጣ​ቸው፤ እር​ሱም ያገ​ለ​ግ​ላ​ቸው ነበር፤ በግ​ዞት ቤትም አንድ ዓመት ተቀ​መጡ።


ዮሴ​ፍም ማልዶ ወደ እነ​ርሱ ገባ፤ እነ​ሆም፥ አዝ​ነው አያ​ቸው።


እነ​ር​ሱም፥ “ሕል​ምን አል​መን የሚ​ተ​ረ​ጕ​ም​ልን አጣን” አሉት። ዮሴ​ፍም አላ​ቸው፥ “ሕል​ምን የሚ​ተ​ረ​ጕም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠው አይ​ደ​ለ​ምን? እስቲ ንገ​ሩኝ፤ ሕል​ማ​ችሁ ምን​ድን ነው?”


እኛም በአ​ን​ዲት ሌሊት ሕል​ምን አለ​ምን፤ እኔና እርሱ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ችን እንደ ሕል​ማ​ችን ትር​ጓሜ አለ​ምን።


እር​ሱም፥ “ቃሌን ስሙ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነቢይ የሆነ ቢኖር በራ​እይ እገ​ለ​ጥ​ለ​ታ​ለሁ፤ ወይም በሕ​ልም እና​ገ​ረ​ዋ​ለሁ።