የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 38:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እን​ደ​ገና ደግሞ ወንድ ልጅን ወለ​ደች፤ ስሙ​ንም ሴሎም ብላ ጠራ​ችው፤ እነ​ር​ሱ​ንም በወ​ለ​ደች ጊዜ ኬሴቢ በሚ​ባል ሀገር ነበ​ረች።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አሁንም ደግማ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሴሎም ብላ አወጣችለት፤ እርሱንም የወለደችው ክዚብ በተባለ ቦታ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አሁንም ደግማ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ሴሎም ብላ አወጣችለት፤ እርሱንም የወለደችው ክዚብ በተባለ ቦታ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንደገናም ወንድ ልጅ ወለደች ስሙንም ሴላ ብላ ጠራችው፤ እርሱንም የወለደችው ይሁዳ አክዚብ በሚባል ቦታ በሚኖርበት ጊዜ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንደ ገና ደግሞ ወንድ ልጅን ወለደች ስሙንም ሴሎም ብላ ጠራችው እርሱንም በወለደች ጊዜ ክዚብ በሚባል አገር ነበረች።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 38:5
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይሁ​ዳም ምራ​ቱን ትዕ​ማ​ርን፥ “ልጄ ሴሎም እስ​ኪ​ያ​ድግ ድረስ በአ​ባ​ትሽ ቤት መበ​ለት ሆነሽ ተቀ​መጪ” አላት፤ እርሱ ደግሞ እንደ ወን​ድ​ሞቹ እን​ዳ​ይ​ሞ​ት​ብኝ ብሎ​አ​ልና። ትዕ​ማ​ርም ሄዳ በአ​ባቷ ቤት ተቀ​መ​ጠች።


ይሁ​ዳም አይቶ “ከእኔ ይልቅ ትዕ​ማር እው​ነ​ተኛ ሆነች፤ ልጄን ሴሎ​ምን አል​ሰ​ጠ​ኋ​ት​ምና” አለ። ትገ​ደል ማለ​ት​ንም ተወ፤ ደግ​ሞም አላ​ወ​ቃ​ትም።


ይሁ​ዳም ለበ​ኵር ልጁ ለዔር ትዕ​ማር የም​ት​ባል ሚስት አጋ​ባው።


የይ​ሁ​ዳም ልጆች፤ ዔር፥ አው​ናን፥ ሴሎም፥ ፋሬስ፥ ዛራ፤ ዔርና አው​ናን በከ​ነ​ዓን ምድር ሞቱ። የፋ​ሬ​ስም ልጆች እኒህ ናቸው፤ ኤስ​ሮም፥ ይሞ​ሔል፤


የይ​ሁዳ ልጆች፤ ዔር፥ አው​ናን፥ ሴሎም፤ እነ​ዚህ ሦስቱ ከከ​ነ​ዓ​ና​ዊቱ ሴት ከሴዋ ልጅ ተወ​ለ​ዱ​ለት። የይ​ሁ​ዳም የበ​ኵር ልጅ ዔር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነበረ፤ ገደ​ለ​ውም።


የይ​ሁ​ዳም ልጅ የሴ​ሎም ልጆች የሌካ አባት ዔር፥ የመ​ሪሳ አባት ለዓዳ፥ ከአ​ስ​ቤዓ ቤት የሚ​ሆኑ ጥሩ በፍታ የሚ​ሠሩ ወገ​ኖች፥


የይ​ሳ​ኮር ልጆች በየ​ወ​ገ​ና​ቸው፤ ከቶላ የቶ​ላ​ው​ያን ወገን፥ ከፉሓ የፉ​ሓ​ው​ያን ወገን፤


ከያ​ሱብ የያ​ሱ​ባ​ው​ያን ወገን፥ ከሥ​ምራ የሥ​ም​ራ​ው​ያን ወገን።