የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 37:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ያዕ​ቆ​ብም ዮሴ​ፍን ከል​ጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወ​ድ​ደው ነበር፤ እርሱ በሽ​ም​ግ​ል​ናው የወ​ለ​ደው ነበ​ርና። በብዙ ኅብር ያጌ​ጠ​ችም ቀሚስ አደ​ረ​ገ​ለት።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እስራኤል ዮሴፍን በስተርጅናው ስለ ወለደው፣ ከልጆቹ ሁሉ አብልጦ ይወድደው ነበር፤ በኅብረ ቀለማት ያጌጠ እጀ ጠባብም አደረገለት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እስራኤልም ዮሴፍን ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወደው ነበር፥ እርሱ በሽምግልናው የወለደው ነበርና፥ በብዙ ኅብር ያጌጠችም ቀሚስ አደረገለት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በስተርጅና የወለደው ስለ ሆነ ያዕቆብ ዮሴፍን ከሌሎች ልጆች ሁሉ አብልጦ ይወደው ነበር፤ ስለዚህም ጌጠኛ የሆነ እጀ ጠባብ ሰፋለት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እስራኤልም ዮሴፍን ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወደው ነበር እርሱ በሽምግልናው የወለደው ነበር በብዙ ኅብር ያጌጠችም ቀሚስ አደረገለት።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 37:3
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዮሴፍ ወደ ወን​ድ​ሞቹ በቀ​ረበ ጊዜ የለ​በ​ሳ​ትን በብዙ ኅብር ያጌ​ጠ​ቺ​ውን ቀሚ​ሱን ገፈ​ፉት፤


የዮ​ሴ​ፍ​ንም ቀሚስ ወሰዱ፤ የፍ​የ​ልም ጠቦት አር​ደው ቀሚ​ሱን በደም ነከ​ሩት።


ብዙ ኅብር ያለ​በ​ትን ቀሚ​ሱ​ንም ላኩ፤ ወደ አባ​ታ​ቸ​ውም አገ​ቡት፤ እን​ዲ​ህም አሉት፥ “ይህን ልብስ አገ​ኘን፤ ይህ የል​ጅህ ልብስ እንደ ሆነ ወይም እን​ዳ​ል​ሆነ እስኪ እየው?”


ብዙ ኅብር ያለ​ው​ንም ልብስ ለብሳ ነበር፤ የን​ጉሡ ልጆች ደና​ግሉ እን​ዲህ ያለ​ውን ልብስ ይለ​ብሱ ነበ​ርና፤ አገ​ል​ጋ​ዩም አስ​ወ​ጥቶ በሩን ዘጋ​ባት።


ከል​ብ​ስ​ሽም ወስ​ደሽ በመ​ርፌ የተ​ጠ​ለፉ ጣዖ​ታ​ትን ሠራሽ፤ አመ​ነ​ዘ​ር​ሽ​ባ​ቸ​ውም፤ ስለ​ዚህ ፈጽ​መሽ አል​ገ​ባ​ሽም፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ እን​ዲህ ያለ ነገር አይ​ሆ​ንም።


አብ ልጁን ይወ​ዳ​ልና፥ ሁሉን በእጁ ሰጠው።


ምር​ኮ​ውን ሲካ​ፈል፥ በኀ​ያ​ላ​ኑም ቸብ​ቸቦ ላይ ወዳ​ጆ​ችን ሲወ​ዳጅ ያገ​ኙት አይ​ደ​ለ​ምን? የሲ​ሣራ ምርኮ በየ​ኅ​ብሩ ነበረ፤ የኅ​ብ​ሩም ቀለም የተ​ለ​ያየ ነበረ፤ የማ​ረ​ከ​ውም ወርቀ ዘቦ ግምጃ በአ​ን​ገቱ ላይ ነበረ።