ዘፍጥረት 37:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፥ “ወንድሞችን እፈልጋለሁ፤ በጎቹን የሚጠብቁበት ወዴት እንደ ሆነ እባክህ ንገረኝ?” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍም፣ “ወንድሞቼን እየፈለግኋቸው ነው፤ መንጎቻቸውን የት እንዳሰማሩ ልትነግረኝ ትችላለህ?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም “ወንድሞቼን እየፈለግሁ ነው፥ በጎቹን የሚጠብቁበት ወዴት እንደሆነ እባክህ ንገረኝ” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍም “ወንድሞቼን እየፈለግሁ ነው፤ መንጋዎቻቸውን ይዘው ወዴት እንደ ተሰማሩ ልትነግረኝ ትችላለህን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም ወንድሞቼን እፈልጋለሁ በጎቹን የሚጠብቁበት ወዴት እንደ ሆነ እባክህ ንገረኝ አለ። |
ሰውየውም፥ “ከዚህ ተነሥተዋል፤ ወደ ዶታይን እንሂድ ሲሉም ሰምቼአቸዋለሁ” አለው። ዮሴፍም ወንድሞቹን ተከታትሎ ሄደ፤ በዶታይንም አገኛቸው።
ነፍሴ የወደደችህ አንተ ንገረኝ፤ በባልንጀሮችህ መንጎች መካከል የተቅበዘበዝሁ እንዳልሆን፥ ወዴት ታሰማራለህ? በቀትርስ ጊዜ ወዴት ትመሰጋለህ?