የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 34:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጋብ​ቾ​ችም ሁኑን፤ ሴቶች ልጆ​ቻ​ች​ሁን ስጡን፤ እና​ን​ተም የእ​ኛን ሴቶች ልጆች ለል​ጆ​ቻ​ችሁ ውሰዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በጋብቻ እንተሳሰር፤ ሴት ልጃችሁን ስጡን፤ የእኛንም ሴቶች አግቡ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከእኛም ጋር በጋብቻ ተሳሰሩ፥ ሴቶች ልጆቻችሁን ስጡን፥ እናንተም የእኛን ሴቶች ልጆች ውሰዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንዲያውም በመካከላችን የጋብቻ ውል እናድርግ፤ እኛ የእናንተን ሴቶች ልጆች እናግባ፤ እናንተም የእኛን ሴቶች ልጆች አግቡ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጋብቾችም ሁኑን፤ ሴቶች ልጆች ስጡን እናንተም የእኛን ሴቶች ልጆች ውሰዱ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 34:9
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሎጥም ወጣ፤ ልጆ​ቹን ለሚ​ያ​ገ​ቡት ለአ​ማ​ቾ​ቹም አላ​ቸው፥ “ተነሡ፤ ከዚች ስፍራ ውጡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህ​ችን ከተማ ያጠ​ፋ​ታ​ልና።” ለአ​ማ​ቾቹ ግን የሚ​ያ​ፌ​ዝ​ባ​ቸው መሰ​ላ​ቸው።


“እጅ​ህን በእጄ ላይ አድ​ርግ፤ እኔም አብሬ ከም​ኖ​ራ​ቸው ከከ​ነ​ዓን ሴቶች ልጆች ለልጄ ለይ​ስ​ሐቅ ሚስት እን​ዳ​ት​ወ​ስ​ድ​ለት በሰ​ማ​ይና በም​ድር አም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ል​ሃ​ለሁ፤


ርብ​ቃም ይስ​ሐ​ቅን አለ​ችው፥ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተ​ነሣ ሕይ​ወ​ቴን ጠላ​ሁት፤ ያዕ​ቆብ ከዚህ ሀገር ሴቶች ልጆች ሚስ​ትን የሚ​ያ​ገባ ከሆነ በሕ​ይ​ወት መኖር ለእኔ ምኔ ነው?”


ከእ​ኛም ጋር ተቀ​መጡ፤ ምድ​ራ​ች​ንም በፊ​ታ​ችሁ ሰፊ ናት፤ ኑሩ​ባት፤ ነግ​ዱም፤ ግዙ​አ​ትም።”


ኤሞ​ርም እን​ዲህ ብሎ ነገ​ራ​ቸው፥ “ልጄ ሴኬም ልጃ​ች​ሁን ወዶ​አ​ታ​ልና ሚስት እን​ድ​ት​ሆ​ነው እር​ስ​ዋን ስጡት።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆ​ችም የሰ​ውን ሴቶች ልጆች መል​ካ​ሞች እን​ደ​ሆኑ አዩ፤ ከመ​ረ​ጡ​አ​ቸ​ውም ሁሉ ሚስ​ቶ​ችን ለራ​ሳ​ቸው ወሰዱ።


ትእ​ዛ​ዝ​ህን እና​ፈ​ርስ ዘንድ ተመ​ል​ሰ​ና​ልና፥ ርኵስ ሥራ ከሚ​ሠሩ ከእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ጋርም ተጋ​ብ​ተ​ና​ልና ከእኛ ከሞት የሚ​ያ​መ​ልጥ እስ​ከ​ማ​ይ​ኖር ድረስ ፈጽ​መህ አት​ቈ​ጣን።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር አት​ጋባ፤ ሴት ልጅ​ህን ለወ​ንድ ልጁ አት​ስጥ፥ ሴት ልጁ​ንም ለወ​ንድ ልጅህ አት​ው​ሰድ።