የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 34:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ልቡ​ና​ውም በያ​ዕ​ቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነ​ደፈ፤ ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱ​ንም ወደ​ዳት፤ ልብ​ዋ​ንም ደስ በሚ​ያ​ሰ​ኛት ነገር ተና​ገ​ራት።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ልቡ በያዕቆብ ልጅ በዲና ተማረከ፤ ልጅቷንም በጣም ወደዳት፤ በጣፈጠም አንደበት አናገራት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነፍሱም በያዕቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነደፈች፥ ልጅቱንም አፈቀራት፥ እርሷንም በአፍቅሮት አናገራት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በውበቷ ተማርኮ እጅግ ወደዳት፤ እርስዋም እንድትወደው ለማድረግ በፍቅር ቃል አነጋገራት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ልቡናውም በያዕቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነደፈ ብላቴናይቱንም ወደዳት ልብዋንም ደስ በሚያስኛት ነገር ተናገራት።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 34:3
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሀ​ገሩ አለቃ የኤ​ዊ​ያ​ዊው ሰው የኤ​ሞር ልጅ ሴኬም አያት፤ ወሰ​ዳ​ትም፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ተኛ፤ አስ​ነ​ወ​ራ​ትም።


ሴኬ​ምም አባ​ቱን ኤሞ​ርን፥ “ይህ​ችን ብላ​ቴና አጋ​ባኝ” ብሎ ነገ​ረው።


አሁ​ንም አት​ፍሩ፤ እኔ እና​ን​ተ​ንና ቤተ ሰቦ​ቻ​ች​ሁን እመ​ግ​ባ​ች​ኋ​ለሁ።” አጽ​ና​ና​ቸ​ውም፤ በል​ባ​ቸው የሚ​ገባ ነገ​ርም ነገ​ራ​ቸው።


አሁ​ንም ተነ​ሥ​ተህ ወጥ​ተህ ለአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በል​ባ​ቸው የሚ​ገባ ነገር ንገ​ራ​ቸው። ዛሬ ወደ እነ​ርሱ ካል​ወ​ጣህ በዚች ሌሊት አንድ ሰው ስንኳ ከአ​ንተ ጋር የሚ​ያ​ድር እን​ዳ​ይ​ኖር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እም​ላ​ለሁ፤ ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትህ ጀምሮ እስ​ከ​ዚች ቀን ድረስ ካገ​ኘህ መከራ ሁሉ ዛሬ የም​ታ​ገ​ኝህ መከራ እን​ድ​ት​ከ​ፋ​ብህ እን​ግ​ዲህ አንተ ለራ​ስህ ዕወቅ” አለው።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ግ​ሎት አስ​ተ​ዋ​ዮች የነ​በ​ሩ​ትን ሌዋ​ው​ያ​ንን ሁሉ ያጽ​ናና ነበር። የደ​ኅ​ን​ነ​ትም መሥ​ዋ​ዕት እያ​ቀ​ረቡ፥ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም አም​ላክ እያ​መ​ሰ​ገኑ ሰባት ቀን በዓል አደ​ረጉ።


ካህ​ናት ሆይ፥ ለኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ወደ ልቧ የሚ​ገባ ነገ​ርን ተና​ገሩ፤ ውር​ደቷ እንደ ተፈ​ጸመ፥ ኀጢ​አ​ቷም እንደ ተሰ​ረየ፥ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅ ስለ ኀጢ​አቷ ሁሉ ሁለት እጥፍ እንደ ተቀ​በ​ለች አጽ​ና​ኑ​አት።


ስለ​ዚህ እነሆ አቅ​በ​ዘ​ብ​ዛ​ታ​ለሁ፤ ወደ ምድረ በዳም አመ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ለል​ብ​ዋም እና​ገ​ራ​ለሁ።


በዚያ ቀን ባሌ ብለሽ ትጠ​ሪ​ኛ​ለሽ እንጂ ዳግ​መኛ በዓ​ሊም ብለሽ አት​ጠ​ሪ​ኝም፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤


ባል​ዋም ተነሣ፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ዕርቅ ሽቶ ወደ እርሱ ሊመ​ል​ሳት ፍለ​ጋ​ዋን ተከ​ትሎ ሄደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አንድ ብላ​ቴና፥ ሁለ​ትም አህ​ዮች ነበሩ። እር​ሱም ወደ አባቷ ቤት ሄደ፤ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት ባየው ጊዜ ደስ ብሎት ተቀ​በ​ለው።


ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው እንደ ገና አለቀሱ፣ ዖርፋም አማትዋን ሳመች፣ ሩት ግን ተጠጋቻት።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት ለሳ​ኦል መን​ገ​ሩን በፈ​ጸመ ጊዜ የዮ​ና​ታን ነፍስ በዳ​ዊት ነፍስ ታሰ​ረች፤ ዮና​ታ​ንም እንደ ነፍሱ ወደ​ደው።