የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 34:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሀ​ገሩ አለቃ የኤ​ዊ​ያ​ዊው ሰው የኤ​ሞር ልጅ ሴኬም አያት፤ ወሰ​ዳ​ትም፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ተኛ፤ አስ​ነ​ወ​ራ​ትም።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሴኬም የተባለው የአገሩ ገዥ የኤዊያዊ የኤሞር ልጅ ባያት ጊዜ ይዞ በማስገደድ ደፈራት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የአገሩ ገዢ የሒዋዊው ሰው የኤሞር ልጅ ሴኬም አያት፥ ወሰዳትም ከእርሷም ጋር ተኛ፥ አስነወራትም።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የአገሩ ገዢ የሒዋዊው የሐሞር ልጅ ሴኬም ባያት ጊዜ ያዛት፤ በማስገደድም ክብረ ንጽሕናዋን ደፈረ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የአገሩ አለቃ የኤዊያዊ ሰው የኤሞር ልጅ ሴኬም አያት ወሰዳርም ከእርስዋም ጋር ተኛ አስነወራትም።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 34:2
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤዌ​ዎ​ንን፥ አሩ​ቄ​ዎ​ንን፥ ኤሴ​ኒ​ዎ​ንን፥


አብ​ር​ሃ​ምም ሚስ​ቱን ሣራን “እኅቴ ናት” አላ​ቸው፤ የከ​ተ​ማ​ዪቱ ሰዎች ስለ እር​ስዋ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ሉት “ሚስቴ” ናት ማለ​ትን ፈር​ቶ​አ​ልና፤ የጌ​ራራ ንጉሥ አቤ​ሜ​ሌ​ክም ላከና ሣራን ወሰ​ዳት።


ድን​ኳ​ኑን ተክ​ሎ​በት የነ​በ​ረ​ው​ንም የእ​ርሻ ክፍል ከሴ​ኬም አባት ከኤ​ሞር ልጆች በመቶ በጎች ገዛው።


የያ​ዕ​ቆብ ልጆ​ችም ወደ ሞቱት ገብ​ተው እኅ​ታ​ቸው ዲናን ያስ​ነ​ወ​ሩ​ባ​ትን ከተ​ማ​ዪ​ቱን ዘረፉ፤


ልቡ​ና​ውም በያ​ዕ​ቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነ​ደፈ፤ ብላ​ቴ​ና​ዪ​ቱ​ንም ወደ​ዳት፤ ልብ​ዋ​ንም ደስ በሚ​ያ​ሰ​ኛት ነገር ተና​ገ​ራት።


ያዕ​ቆ​ብም ስም​ዖ​ን​ንና ሌዊን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “ክፉ አደ​ረ​ጋ​ች​ሁ​ብኝ፤ በዚች ሀገር በሚ​ኖሩ በከ​ነ​ዓ​ና​ው​ያ​ንና በፌ​ር​ዜ​ዎ​ና​ው​ያን ሰዎች ዘንድ አስ​ጠ​ላ​ች​ሁኝ። እኔ በቍ​ጥር ጥቂት ነኝ፤ እነ​ርሱ በእኔ ላይ ይሰ​በ​ሰ​ቡና ይወ​ጉ​ኛል፤ እኔና ቤቴም እን​ጠ​ፋ​ለን።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆ​ችም የሰ​ውን ሴቶች ልጆች መል​ካ​ሞች እን​ደ​ሆኑ አዩ፤ ከመ​ረ​ጡ​አ​ቸ​ውም ሁሉ ሚስ​ቶ​ችን ለራ​ሳ​ቸው ወሰዱ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ወደ ማታ ጊዜ ዳዊት ከም​ን​ጣፉ ተነሣ፤ በን​ጉ​ሥም ቤት በሰ​ገ​ነት ላይ ተመ​ላ​ለሰ፤ በሰ​ገ​ነ​ቱም ሳለ አን​ዲት ሴት ስት​ታ​ጠብ አየ፤ ሴቲ​ቱም እጅግ የተ​ዋ​በች መልከ መል​ካም ነበ​ረች።


ዳዊ​ትም መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ልኮ አስ​መ​ጣት፤ ወደ እር​ሱም ገባች፤ ከር​ኵ​ሰ​ቷም ነጽታ ነበ​ርና ከእ​ር​ስዋ ጋር ተኛ፤ ወደ ቤቷም ተመ​ለ​ሰች።


አም​ኖ​ንም ቃል​ዋን አል​ሰ​ማም፤ ይዞም አደ​ከ​ማት፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ጋር ተኛ።


“ከዐ​ይኔ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረ​ግሁ፥ ድን​ግ​ሊ​ቱ​ንም አል​ተ​መ​ለ​ከ​ት​ሁም፤


ልቤ ወደ ሌላ ወንድ ሚስት ተከ​ትሎ እንደ ሆነ፥ በደ​ጅ​ዋም አድ​ብቼ እንደ ሆነ፥


ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፤ ከአላዋቂዎች ጋር የሚሄድ ግን አላዋቂ ይሆናል።


እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል።


ከዚ​ያም በኋላ በእ​ር​ስዋ ደስ ባይ​ልህ አር​ነት አው​ጥ​ተህ ትለ​ቅ​ቃ​ታ​ለህ፤ በዋጋ ግን አት​ሸ​ጣ​ትም፤ አግ​ብ​ተ​ሃ​ታ​ልና እን​ደ​ባ​ሪያ አት​ቍ​ጠ​ራት።


ብላ​ቴ​ና​ዪቱ በከ​ተማ ውስጥ ሳለች አል​ጮ​ኸ​ች​ምና፥ ሰው​የ​ውም የባ​ል​ጀ​ራ​ውን ሚስት አስ​ነ​ው​ሮ​አ​ልና በድ​ን​ጋይ ወግ​ረው ይግ​ደ​ሉ​አ​ቸው፤ እን​ዲሁ ክፉ​ውን ነገር ከው​ስ​ጥህ ታስ​ወ​ግ​ዳ​ለህ።


ያ የደ​ፈ​ራት ሰው አምሳ የብር ሰቅል ለብ​ላ​ቴ​ና​ዪቱ አባት ይስጥ፤ አስ​ነ​ው​ሮ​አ​ታ​ልና ሚስት ትሁ​ነው፤ በዕ​ድ​ሜ​ውም ዘመን ሁሉ ሊፈ​ታት አይ​ገ​ባ​ውም።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ኤዌ​ዎ​ና​ው​ያ​ንን፥ “ምና​ል​ባት በመ​ካ​ከ​ላ​ችን የም​ት​ቀ​መጡ እንደ ሆነ እን​ዴ​ትስ ከእ​ና​ንተ ጋር ቃል ኪዳን እና​ደ​ር​ጋ​ለን?” አሉ​አ​ቸው።


ሶም​ሶ​ንም ወደ ቴም​ናታ ወረደ፤ በቴ​ም​ና​ታም ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ልጆች አን​ዲት ሴት አየ፤ እር​ስ​ዋም በፊቱ ደስ አለ​ችው።


የአ​ቤ​ድም ልጅ ገዓል፥ “አቤ​ሜ​ሌክ ማን ነው? እን​ገ​ዛ​ለ​ትስ ዘንድ የሴ​ኬም ልጅ ማን ነው? እርሱ የይ​ሩ​በ​ኣል ልጅ አይ​ደ​ለ​ምን? ዜቡ​ልስ የእ​ርሱ ጠባቂ አይ​ደ​ለ​ምን? ከሴ​ኬም አባት ከኤ​ሞር ሰዎች ጋርስ አገ​ል​ጋዩ አይ​ደ​ለ​ምን? ስለ​ም​ንስ ለዚህ እን​ገ​ዛ​ለን?