የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 34:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለያ​ዕ​ቆብ የተ​ወ​ለ​ደች የልያ ልጅ ዲናም የዚ​ያን ሀገር ሴቶች ልጆ​ችን ለማ​የት ወጣች።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ልያ ለያዕቆብ የወለደችለት ሴት ልጅ ዲና፣ አንድ ቀን የዚያን አገር ሴቶች ለማየት ወጣች።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የልያ ልጅ ዲናም፥ የዚያን አገር ሴት ልጆችን ለማየት ወጣች።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዕለታት አንድ ቀን ልያ ለያዕቆብ የወለደችለት ዲና በዚያ አካባቢ የሚኖሩትን ከነዓናውያት ሴቶች ለማየት ወጣች፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለያዕቆብ የወለደችለት የልያ ልጅ ዲናም የዚያን አገር ሴቶች ልጆችን ለማየት ወጣች።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 34:1
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዔሳ​ውም አርባ ዓመት ሲሆ​ነው የኬ​ጢ​ያ​ዊው የብ​ኤ​ልን ልጅ ዮዲ​ትን፥ የኬ​ጢ​ያ​ዊው የኤ​ሎ​ንን ልጅ ቤሴ​ሞ​ት​ንም ሚስ​ቶች አድ​ርጎ አገባ፤


ርብ​ቃም ይስ​ሐ​ቅን አለ​ችው፥ “ከኬጢ ሴቶች ልጆች የተ​ነሣ ሕይ​ወ​ቴን ጠላ​ሁት፤ ያዕ​ቆብ ከዚህ ሀገር ሴቶች ልጆች ሚስ​ትን የሚ​ያ​ገባ ከሆነ በሕ​ይ​ወት መኖር ለእኔ ምኔ ነው?”


ዔሳ​ውም ይስ​ሐቅ ያዕ​ቆ​ብን እንደ ባረ​ከው በአየ ጊዜ ከዚ​ያም ሚስ​ትን ያገባ ዘንድ ወደ ሁለቱ የሶ​ርያ ወን​ዞች መካ​ከል እንደ ላከው፥ በባ​ረ​ከ​ውም ጊዜ፥ “ከከ​ነ​ዓን ሴቶች ልጆች ሚስ​ትን አታ​ግባ” ብሎ እን​ዳ​ዘ​ዘው፥


ልያም፥ “እኔ ብፅ​ዕት ነኝ፤ ሴቶች ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ኛ​ልና” አለች፤ ስሙ​ንም አሴር ብላ ጠራ​ችው።


ከዚ​ያም በኋላ ሴት ልጅን ወለ​ደች፤ ስም​ዋ​ንም ዲና አለ​ቻት።


በዚ​ያም መሠ​ው​ያ​ዉን አቆመ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም አም​ላክ ጠራ።


ልያ በመ​ስ​ጴ​ጦ​ምያ በሶ​ርያ ለያ​ዕ​ቆብ የወ​ለ​ደ​ቻ​ቸው ልጆ​ችና ሴቲቱ ልጅዋ ዲና እነ​ዚህ ናቸው፤ ወን​ዶ​ችም ሴቶ​ችም ልጆ​ችዋ ሁሉ ሠላሳ አራት ነፍስ ናቸው።


መን​ገ​ድ​ሽን እጥፍ ታደ​ርጊ ዘንድ ለምን እጅግ ትሮ​ጫ​ለሽ? በአ​ሦር እን​ዳ​ፈ​ርሽ በግ​ብ​ፅም ታፍ​ሪ​ያ​ለሽ።


ከዚህም ጋር ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራን መፍታት ደግሞ ይማራሉ፤ የማይገባውንም እየተናገሩ ለፍላፊዎችና በነገር ገቢዎች ይሆናሉ እንጂ፥ ሥራ ፈቶች ብቻ አይደሉም።