የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 33:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዕቁ​ባ​ቶ​ቹ​ንና ልጆ​ቻ​ቸ​ው​ንም በፊት አደ​ረገ፤ ልያ​ንና ልጆ​ች​ዋን በኋላ፥ ራሔ​ል​ንና ዮሴ​ፍ​ንም ከሁሉ በኋላ አደ​ረገ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ሁለቱን አገልጋዮች ከነልጆቻቸው አስቀደመ፤ ልያንና ልጆቿንም አስከተለ፤ ራሔልንና ዮሴፍን ግን ከሁሉ ኋላ እንዲሆኑ አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሴት አገልጋዮቹንና ልጆቻቸውንም ከፊት አደረገ፥ ልያንና ልጆችዋንም አስከተለ፥ ከዚያም ራሔልንና ዮሴፍን ከሁሉ በኋላ አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በመጀመሪያ ሁለቱን ሴቶች አገልጋዮቹንና ልጆቻቸውን አስቀደመ፤ ቀጥሎ ልያንና ልጆችዋን አስከተለ፤ በመጨረሻም ራሔልንና ዮሴፍን ከሁሉ በኋላ አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ባሪያዎችንና ልጆቻቸውንም በፊት አደረገ ልያንና ልጆችዋንም በኋለኛው ስፍራ ራሔልንና ዮሴፍንም ከሁሉ በኍላ አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 33:2
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለላ​ባም ሁለት ሴቶች ልጆች ነበ​ሩት፤ የታ​ላ​ቂቱ ስም ልያ የታ​ና​ሺ​ቱም ስም ራሔል ነበረ።


ያዕ​ቆ​ብም ወደ ራሔል ደግሞ ገባ። ራሔ​ል​ንም ከልያ ይልቅ ወደ​ዳት፤ ሌላ ሰባት ዓመ​ትም ተገ​ዛ​ለት።


ያዕ​ቆ​ብም ዐይ​ኑን አነሣ፤ እነ​ሆም፥ ዔሳ​ውን ሲመጣ አየው፤ ከእ​ር​ሱም ጋር አራት መቶ ሰዎች ነበሩ፤ ልጆ​ቹ​ንም ከፍሎ ወደ ልያና ወደ ራሔል ወደ ሁለ​ቱም ዕቁ​ባ​ቶቹ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤


እር​ሱም በፊ​ታ​ቸው አለፈ፤ ወደ ወን​ድሙ ወደ ዔሳ​ውም እስ​ኪ​ደ​ርስ ድረስ ወደ ምድር ሰባት ጊዜ ሰገደ።


ያዕ​ቆ​ብም ዮሴ​ፍን ከል​ጆቹ ሁሉ ይልቅ ይወ​ድ​ደው ነበር፤ እርሱ በሽ​ም​ግ​ል​ናው የወ​ለ​ደው ነበ​ርና። በብዙ ኅብር ያጌ​ጠ​ችም ቀሚስ አደ​ረ​ገ​ለት።


እና​ታ​ችሁ እጅግ ታፍ​ራ​ለች፤ የወ​ለ​ደ​ቻ​ች​ሁም ትጐ​ሰ​ቍ​ላ​ለች፤ እነሆ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ኋለ​ኛ​ዪቱ ትሆ​ና​ለች፤ ምድረ በዳና ደረቅ ምድር፥ በረ​ሀም ትሆ​ና​ለች።


እኔ በምሠራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር፥ እንዲሁ እምራቸዋለሁ።