የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 25:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አብ​ር​ሃ​ምም በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ ለልጁ ለይ​ስ​ሐቅ ሰጠው፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አብርሃም ያለውን ሀብት ሁሉ ለይሥሐቅ አወረሰው፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አብርሃምም የነበረውን ሁሉ ለይስሐቅ ሰጠው፥

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አብርሃም ያለውን ሀብት ሁሉ ለይስሐቅ አወረሰው፤

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አብርሃምም የነበረውን ሁሉ ለይስሐቅ ሰጠው፤

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 25:5
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጌታ​ዬን እጅግ ባረ​ከው፤ አገ​ነ​ነ​ውም፤ ላሞ​ች​ንና በጎ​ችን፥ ወር​ቅ​ንና ብርን፥ ወን​ዶች ባሪ​ያ​ዎ​ች​ንና ሴቶች ባሪ​ያ​ዎ​ችን፥ ግመ​ሎ​ች​ንና አህ​ዮ​ች​ንም ሰጠው።


የጌ​ታዬ የአ​ብ​ር​ሃም ሚስት ሣራም በእ​ር​ጅ​ናዋ ለጌ​ታዬ ወንድ ልጅን ወለ​ደች፤ የነ​በ​ረ​ው​ንም ሁሉ ሰጠው።”


የም​ድ​ያ​ምም ልጆች ጌፌር፥ ዔፋር፥ ሄኖኅ፥ አቢ​ሮ​ንና ቲያ​ሮስ ናቸው። እነ​ዚ​ህም ሁሉ የኬ​ጡራ ልጆች ናቸው።


ወን​ዶ​ችና ሴቶች አገ​ል​ጋ​ዮ​ችን፥ ብዙ በጎ​ች​ንና ላሞ​ችን፥ የእ​ርሻ መሬ​ት​ንም ገዛ፤ የፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ሰዎ​ችም ቀኑ​በት።


ነፍ​ሴን ተመ​ል​ክ​ተህ ተቤ​ዣት፤ ስለ ጠላ​ቶ​ችም አድ​ነኝ።


ሁሉ ከአባቴ ዘንድ ተሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድም በቀር ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም።


ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።


ሥጋ በለ​በ​ሰው ሁሉ ላይ ሥል​ጣ​ንን እንደ ሰጠ​ኸው መጠን ለሰ​ጠ​ኸው ሁሉ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ቸው ዘንድ።


አብ ልጁን ይወ​ዳ​ልና፥ ሁሉን በእጁ ሰጠው።


እና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ከሆን ወራ​ሾቹ ነን፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወራ​ሾች ከሆ​ንም የክ​ር​ስ​ቶስ ወራ​ሾቹ ነን፤ በመ​ከራ ከመ​ሰ​ል​ነ​ውም በክ​ብር እን​መ​ስ​ለ​ዋ​ለን።


ለልጁ ስንኳ አል​ራ​ራም፤ ስለ ሁላ​ችን ቤዛ አድ​ርጎ አሳ​ልፎ ሰጠው እንጂ፥ እን​ግ​ዲህ እርሱ ሁሉን እን​ዴት አይ​ሰ​ጠ​ንም?


ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ከሆ​ና​ች​ሁም እን​ግ​ዲህ ተስ​ፋ​ውን የም​ት​ወ​ርሱ የአ​ብ​ር​ሃም ዘር እና​ንተ ናችሁ።


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ እኛስ እንደ ይስ​ሐቅ የተ​ስፋ ልጆች ነን።


ሁሉ በእ​ርሱ ፍጹም ሆኖ ይኖር ዘንድ፥ ወዶ​አ​ልና።


በኋላ ዘመን ግን ሁሉን ወራሽ ባደ​ረ​ገው፥ ሁሉ​ንም በፈ​ጠ​ረ​በት በልጁ ነገ​ረን።