እንስራሽን አዘንብለሽ ውኃ አጠጭኝ የምላት እርስዋም፦ ‘አንተ ጠጣ፥ ግመሎችህን ደግሞ እስኪረኩ አጠጣለሁ’ የምትለኝ ድንግል፥ እርስዋ ለባሪያህ ለይስሐቅ ያዘጋጀሃት ትሁን፤ በዚህም ለጌታዬ ለአብርሃም ምሕረትን እንዳደረግህ አውቃለሁ።”
ዘፍጥረት 24:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱንም ከአጠጣች በኋላ፦ “ለግመሎችህ ደግሞ ሁሉም እስኪረኩ ድረስ ውኃ እቀዳለሁ” አለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱን ካጠጣችው በኋላ፣ “ግመሎችህም ጠጥተው እስኪጠግቡ ድረስ ውሃ እቀዳላቸዋለሁ” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱንም ካጠጣች በኋላ፦ “ለግመሎችህ ደግሞ ሁሉም እስኪረኩ ድረስ ውኃ እቀዳለሁ” አለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠጥቶም ከረካ በኋላ “ለግመሎችህም ውሃ እቀዳላቸዋለሁ፤ እስኪበቃቸውም ድረስ ይጠጡ” አለችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱንም ካጠጣች በኍላ፦ ለግመሎችህ ደግሞ ሁሉም እስኪረኩ ድረስ ውኃ እቀዳለሁ አለች። |
እንስራሽን አዘንብለሽ ውኃ አጠጭኝ የምላት እርስዋም፦ ‘አንተ ጠጣ፥ ግመሎችህን ደግሞ እስኪረኩ አጠጣለሁ’ የምትለኝ ድንግል፥ እርስዋ ለባሪያህ ለይስሐቅ ያዘጋጀሃት ትሁን፤ በዚህም ለጌታዬ ለአብርሃም ምሕረትን እንዳደረግህ አውቃለሁ።”
ፈጥናም ውኃውን ከእንስራዋ በማጠጫው ውስጥ ገለበጠችው፤ ደግሞም ልትቀዳ ወደ ጕድጓዱ ሮጠች፤ ለግመሎቹም ሁሉ ውኃ ቀዳች።