የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 22:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አብ​ር​ሃ​ምም የመ​ሥ​ዋ​ዕ​ቱን ዕን​ጨት አን​ሥቶ ለልጁ ለይ​ስ​ሐቅ አሸ​ከ​መው፤ እር​ሱም እሳ​ቱ​ንና ቢላ​ዋ​ዉን በእጁ ያዘ፤ ሁለ​ቱም አብ​ረው ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አብርሃም ለሚቃጠል መሥዋዕት የሚሆነውን ዕንጨት ወስዶ፣ ልጁን ይሥሐቅን አሸከመው፤ እሳቱንና ቢላዋውንም ራሱ ያዘ። ሁለቱም ዐብረው ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አብርሃምም የመሥዋዕቱን ማቃጠያ እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፥ እርሱም እሳቱንና ቢላዋውን በእጁ ያዘ፥ ከዚያም ሁለቱ አብረው ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አብርሃምም የመሥዋዕቱን እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፤ እርሱ ግን ቢለዋውንና እሳቱን ያዘ፤ ሁለቱም አብረው ሲሄዱ ሳለ፥

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አብርሃምም የመሥዋዕቱን እንጨት አንሥቶ ለልጁ ለይስሐቅ አሸከመው፤ እርሱም እሳቱንና ቢላዋውን በእጁ ያዘ፥ ሁለቱም አብረው ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 22:6
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አብ​ር​ሃ​ምም ሎሌ​ዎ​ቹን አላ​ቸው፥ “አህ​ያ​ውን ይዛ​ችሁ በዚህ ቈዩ፤ እኔና ልጄ ወደ​ዚያ ተራራ ሄደን እን​ሰ​ግ​ዳ​ለን፤ ሰግ​ደ​ንም ወደ እና​ንተ እን​መ​ለ​ሳ​ለን።”


ኤል​ያ​ስም ኤል​ሳ​ዕን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ ዮር​ዳ​ኖስ ልኮ​ኛ​ልና እባ​ክህ፥ በዚህ ቈይ” አለው። ኤል​ሳ​ዕም፥ “ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ሕያው ነፍ​ስ​ህ​ንም አል​ለ​ይ​ህም” አለው፤ ሁለ​ቱም ሄዱ።


እኛ ሁላ​ችን እንደ በጎች ተቅ​በ​ዝ​ብ​ዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያ​ን​ዳ​ንዱ ወደ ገዛ መን​ገዱ አዘ​ነ​በለ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ኀጢ​አ​ታ​ችን ለሞት አሳ​ልፎ ሰጠው።


መስ​ቀ​ሉ​ንም ተሸ​ክሞ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ጎል​ጎታ ወደ ተባ​ለው ቀራ​ንዮ ወደ​ሚ​ባል ቦታ ወጣ።


ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።