እርሱም አለው፥ “የሦስት ዓመት ላም፥ የሦስት ዓመት ፍየልም፥ የሦስት ዓመት በግም፥ ዋኖስም፥ ርግብም አምጣ፤ እኒህንም ሁሉ አምጥተህ ከሁለት ከሁለት ቍረጣቸው፤ ወፎችን ግን አትቍረጣቸው።”
ዘፍጥረት 15:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደምወርሳት በምን አውቃለሁ?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብራምም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህችን ምድር እንደምወርሳት በምን ዐውቃለሁ?” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ፥ እንድወርሳት በምን አውቃለሁ? አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብራም ግን “ጌታ አምላክ ሆይ፥ ይህች ምድር የእኔ እንደምትሆን እንዴት ለማወቅ እችላለሁ?” ሲል ጠየቀ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ እንድወርሳት በምን አውቃለሁ? አለ። |
እርሱም አለው፥ “የሦስት ዓመት ላም፥ የሦስት ዓመት ፍየልም፥ የሦስት ዓመት በግም፥ ዋኖስም፥ ርግብም አምጣ፤ እኒህንም ሁሉ አምጥተህ ከሁለት ከሁለት ቍረጣቸው፤ ወፎችን ግን አትቍረጣቸው።”
ስደተኛ ሆነህ የተቀመጥህባትን፥ እግዚአብሔር ለአብርሃም የሰጣትን ምድር ትወርስ ዘንድ የአባቴን የአብርሃምን በረከት ለአንተ ይስጥህ፤ ከአንተም በኋላ ለዘርህ።”
ዮሴፍም ወንድሞቹን አላቸው፥ “እኔ እሞታለሁ፤ እግዚአብሔርም መጐብኘትን ይጐበኛችኋል፤ ከዚህችም ምድር ያወጣችኋል። ለአባቶቻችን ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደ ማለላቸው ምድር ያገባችኋል።”
ሕዝቅያስም ኢሳይያስን፥ “እግዚአብሔር እንዲፈውሰኝ፥ እኔስ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንድወጣ ምልክቱ ምንድን ነው?” አለው።
ቃል ኪዳኔን የተላለፉትን ሰዎች፥ በፊቴ ያደረጉትን ቃል ኪዳን ያልፈጸሙትን፥ እንቦሳውንም ቈርጠው በቍራጩ መካከል ያለፉትን አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።
የይሁዳን አለቆችና የኢየሩሳሌምን አለቆች፥ ጃንደረቦችንና ካህናትንም፥ በእንቦሳም ቍራጭ መካከል ያለፉትን የሀገሩን ሕዝብ ሁሉ፥
ዘካርያስም የእግዚአብሔርን መልአክ እንዲህ አለው፥ “ይህ እንደሚሆን በምን አውቃለሁ? እነሆ፥ እኔ አርጅችአለሁ፤ የሚስቴም ዘመንዋ አልፏል።”