የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፍጥረት 14:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከኤ​ላም ንጉሥ ከኮ​ሎ​ዶ​ጎ​ሞር፥ ከአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ ከቴ​ሮ​ጋል፥ ከሰ​ና​ዖር ንጉሥ ከአ​ሜ​ሮ​ፌል፥ ከእ​ላ​ሳር ንጉሥ ከአ​ር​ዮክ ጋር ተጋ​ጠሙ። እነ​ዚህ አራቱ ነገ​ሥ​ታት ከአ​ም​ስቱ ነገ​ሥ​ታት ጋር ተዋጉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነዚህ ዐምስቱ፣ በኤላም ንጉሥ በኮሎዶጎምር፣ በጎይም ንጉሥ በቲድዓል፣ በሰናዖር ንጉሥ በአምራፌል፣ በእላሳር ንጉሥ በአርዮክ፣ በእነዚህ በአራቱ ላይ ዘመቱባቸው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የኤላምን ንጉሥ ኮሎዶጎምርን፥ የአሕዛብን ንጉሥ ቲድዓልን፥ የሰናዖርን ንጉሥ አምራፌልን፥ የእላሳርን ንጉሥ አርዮክን ለመውጋት አምስቱ ነገሥታት በእነዚህ በአራቱ ላይ ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የተዋጉትም ከዔላም፥ ከጎይም፥ ከባቢሎንና ከኤላሳር ነገሥታት ጋር ነበር፤ አምስቱ ነገሥታት ከአራቱ ነገሥታት ጋር የተዋጉት በዚህ ዐይነት ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የኤላምን ንጉሥ ኮሎዶጎምርን፤ የአሕዛብን ንጉሥ ቲድዓልን፤ የሰናዖርን ንጉሥ አምራፌልን፥ የእላሳርን ንጉሥ አርዮክን ለመውጋት አምስቱ ነገሥታት በእነዚህ በአራቱ ላይ ወጡ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፍጥረት 14:9
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሴ​ምም ልጆች ኤላም፥ አሦር፥ አር​ፋ​ክ​ስድ፥ ሉድ፥ አራም፥ ቃይ​ናን።


በሰ​ና​ዖር ንጉሥ በአ​ሚ​ሮ​ፌል፥ በእ​ላ​ሳር ንጉሥ በአ​ር​ዮክ፥ በኤ​ላም ንጉሥ በኮ​ሎ​ዶ​ጎ​ሞር፥ በአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ በቴ​ሮ​ጋል ዘመን እን​ዲህ ሆነ፤


ያም የጨው ሸለቆ የዝ​ፍት ጕድ​ጓ​ዶች ነበ​ሩ​በት። የሰ​ዶም ንጉ​ሥና የገ​ሞራ ንጉ​ሥም ሸሹና በዚያ ወደቁ፤ የቀ​ሩ​ትም ወደ ተራ​ራ​ማው ሀገር ሸሹ።


የሰ​ዶም ንጉ​ሥና የገ​ሞራ ንጉሥ፥ የአ​ዳማ ንጉ​ሥና የሲ​ባ​ዮን ንጉሥ፥ ሴጎር የተ​ባ​ለች የባ​ላቅ ንጉ​ሥም ወጡ፤ እነ​ዚህ ሁሉ በጨው ሸለቆ በእ​ነ​ርሱ ላይ ለሰ​ልፍ ወጡ፤


በይ​ሁዳ ንጉሥ በሴ​ዴ​ቅ​ያስ በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ዓመተ መን​ግ​ሥት ስለ ኤላም ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው።