የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘፀአት 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ይህ በእ​ጅህ ያለው ምን​ድን ነው?” አለው። እር​ሱም፥ “በትር ነው” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔርም፣ “በእጅህ የያዝሃት እርሷ ምንድን ናት?” ሲል ጠየቀው። እርሱም መልሶ፣ “በትር ናት” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም፦ “ይህ በእጅህ ያለው ምንድነው?” አለው። እርሱም፦ “በትር ነው” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔርም “በእጅህ የያዝከው ምንድን ነው?” አለው። እርሱም “በትር ነው” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም፦ “ይህች በእጅህ ያለችው ምንድር ናት?” አለው። እርሱም፦ “በትር ናት፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘፀአት 4:2
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያዕ​ቆ​ብም ልብን፥ ለውዝ፥ ኤር​ሞን ከሚ​ባሉ ዕን​ጨ​ቶች ርጥብ በት​ርን ወስዶ በበ​ት​ሮቹ ውስጥ ያለው ነጭ እን​ዲ​ታይ ነጭ ሽመ​ል​መሌ አድ​ርጎ ላጣ​ቸው።


ኤል​ሳ​ዕም፥ “አደ​ር​ግ​ልሽ ዘንድ ምን ትሻ​ለሽ? በቤ​ት​ሽም ያለ​ውን ንገ​ሪኝ” አላት። እር​ስ​ዋም፥ “ለእኔ ለአ​ገ​ል​ጋ​ይህ ከዘ​ይት ማሰሮ በቀር በቤቴ አን​ዳች የለ​ኝም” አለ​ችው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ ታላቅ ናት፥ በፈ​ቃ​ዱም ሁሉ የተ​ፈ​ለ​ገች ናት።


ይህ​ች​ንም ተአ​ም​ራት የም​ታ​ደ​ር​ግ​ባ​ትን በትር በእ​ጅህ ያዝ።”


ሙሴም ሚስ​ቱ​ንና ልጆ​ቹን ወሰደ፤ በአ​ህ​ዮች ላይም አስ​ቀ​መ​ጣ​ቸው፤ ወደ ግብ​ፅም ሀገር ተመ​ለሰ፤ ሙሴም ያችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በትር በእጁ ይዞ ሄደ።


ማል​ደህ ወደ ፈር​ዖን ሂድ፤ እነሆ፥ ወደ ውኃ ይወ​ጣል፤ ትገ​ና​ኘ​ውም ዘንድ አንተ በወ​ንዝ ዳር ትቆ​ማ​ለህ፤ እባ​ብም ሆና የተ​ለ​ወ​ጠ​ች​ዉን በትር በእ​ጅህ ትወ​ስ​ዳ​ለህ።


“ፈር​ዖን፦ ተአ​ም​ራ​ት​ንና ድን​ቅን አሳ​ዩኝ ሲላ​ችሁ፥ ወን​ድ​ምህ አሮ​ንን፦ ‘በት​ር​ህን ወስ​ደህ በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ፊት ጣላት’ በለው፤ እባ​ብም ትሆ​ና​ለች።”


ነገር ግን ለድ​ሆች በጽ​ድቅ ይፈ​ር​ዳል፤ ለም​ድ​ርም የዋ​ሆች በቅ​ን​ነት ይበ​ይ​ናል፤ በአ​ፉም ቃል ምድ​ርን ይመ​ታል፤ በከ​ን​ፈ​ሩም እስ​ት​ን​ፋስ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ውን ያጠ​ፋ​ዋል።


ከበ​ሬም ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ፥ ከበ​ግም ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ፥ ከእ​ረ​ኛ​ውም በትር በታች ከሚ​ያ​ልፍ ሁሉ ከዐ​ሥር አንድ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ቀ​ደሰ ይሆ​ናል።


በቀርሜሎስ መካከል ባለው ዱር ብቻቸውን የተቀመጡት ሰዎችህ፥ የርስትህን በጎች፥ በበትርህ አግድ፥ እንደ ቀደመውም ዘመን በበሳንና በገለዓድ ይሰማሩ።