ከእነርሱም አንዲቱ መንገድ ዐላፊውን ብታስተውና አብራው ብትተኛ፥ እንደ እርስዋ ዝግጁ ሆና አልተገኘችምና፥ መቀነቷም አልተፈታላትምና ይህችኛዋ ሌላዋን ትነቅፋታለች። ለእነርሱ የሚደረገው ሁሉ ሐሰት ነው፤ እንደ አማልክት ሊቈጥሯቸው፥ አማልክትም ሊሉአቸው እንዴት ይቻላል?