እናንተ ግን ኀጢአት እስክታልፍ ድረስ ደጅ ጥኑ። ስማቸው ቅዱሳን ከተጻፉበት መጽሐፍ ይፋቅ ዘንድ አለውና፥ ዘራቸውም ለዘላለም ይጠፋልና። ልጆቻቸውም ይሞታሉ፥ በማይታይም ምድረ በዳ ጮኸው ያለቅሳሉ፤ በእሳትም ይቃጠላሉ፥ በዚያ ምድር የለምና። ከጥልቅነቱ የተነሣ ወደ ላይ ማየትን አልቻልሁምና በዚያ ቦታ እንደማይታይ ደመና ያለ ነገርን አየሁ።