የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘዳግም 26:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጸ​ናች እጅና በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፥ በታ​ላ​ቅም ግርማ፥ በታ​ላቅ ተአ​ም​ራ​ትም፥ በድ​ን​ቅም ከግ​ብፅ አወ​ጣን፤

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚህ የተነሣ እግዚአብሔር በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ፣ በታላቅ ድንጋጤ፣ በታምራዊ ምልክትና በድንቅ ከግብጽ አወጣን።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም በብርቱ እጅና በተዘረጋች ክንድ፥ በታላቅ ድንጋጤ፥ በተአምራትና በድንቅም ጌታ ከግብጽ አወጣን።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔርም በታላቅ ኀይሉና ሥልጣኑ ታላቅ ፍርሀትን በማሳደር፥ ሥራዎችን ተአምራትንና ድንቅ ሥራዎችን በማሳየት ከግብጽ አወጣን።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በታላቅም ድንጋጤ፥ በተአምራትም፥ በድንቅም ከግብፅ አወጣን፤

ምዕራፉን ተመልከት



ዘዳግም 26:8
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ከራ​ምሴ ተነ​ሥ​ተው ወደ ሱኮት ሄዱ፤ ከጓዝ ጋር ካሉት ሌላ ስድ​ስት መቶ ሺህ ሰው የሚ​ያ​ህል እግ​ረኛ ነበረ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ አራት መቶ ሠላሳ ዓመት ከተ​ፈ​ጸመ በኋላ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሠራ​ዊት ሁሉ በሌ​ሊት ከግ​ብፅ ምድር ወጣ።


በዚ​ያም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች ከሠ​ራ​ዊ​ታ​ቸው ጋር ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣ​ቸው።


ሙሴም ሕዝ​ቡን አለ፥ “ከባ​ር​ነት ቤት ከግ​ብፅ የወ​ጣ​ች​ሁ​ባ​ትን ይህ​ችን ቀን ዐስቡ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከዚህ ቦታ በበ​ረ​ታች እጅ አው​ጥ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና። ስለ​ዚህ የቦካ እን​ጀራ አት​ብሉ።


ስለ​ዚ​ህም ፈጥ​ነህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ በላ​ቸው፥ “እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ተገ​ዥ​ነት አወ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከባ​ር​ነ​ታ​ቸ​ውም አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፤ በታ​ላቅ ፍር​ድም እታ​ደ​ጋ​ች​ኋ​ለሁ፤


በሙ​ሴም ቀኝ እጅ ውኃ​ውን ከፈ​ልሁ፤” ውኃ​ውም ተከ​ፍሎ በፊቱ ጸና፤ የዘ​ለ​ዓ​ለም ስም​ንም አደ​ረ​ገ​ለት።


በም​ል​ክ​ትና በድ​ንቅ ነገር፥ በብ​ርቱ እጅና በተ​ዘ​ረ​ጋች ክንድ፥ በታ​ላ​ቅም ግርማ ሕዝ​ብ​ህን እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣህ።


በግ​ብፅ ምድር በፈ​ር​ዖ​ንና በሹ​ሞቹ ሁሉ ላይ፥ በም​ድ​ሪ​ቱም ሁሉ ላይ ምል​ክ​ት​ንና ድን​ቅን ያደ​ርግ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ላከው ያለ፥


በእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ ፊት በታ​ላቅ ተአ​ምር ሁሉና በጸ​ናች እጅ፥ በተ​ዘ​ረ​ጋ​ችም ክንድ ሁሉ እን​ዳ​ደ​ረ​ገው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ አል​ተ​ነ​ሣም።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዐ​ይ​ና​ችሁ ፊት በግ​ብፅ ለእ​ና​ንተ እንደ ሠራው ሁሉ ፥ በፈ​ተ​ናና በተ​አ​ም​ራት፥ በድ​ን​ቅና በሰ​ልፍ፥ በጸ​ናች እጅና በተ​ዘ​ረጋ ክንድ፥ በታ​ላ​ቅም ማስ​ፈ​ራ​ራት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሌላ ሕዝብ መካ​ከል ገብቶ ለእ​ርሱ ሕዝ​ብን ይወ​ስድ ዘንድ ሞክሮ እንደ ሆነ፥


አን​ተም በግ​ብፅ ባሪያ እንደ ነበ​ርህ አስብ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ በጸ​ናች እጅና በተ​ዘ​ረጋ ክንድ ከዚያ አወ​ጣህ፤ ስለ​ዚህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ ዕለተ ሰን​በ​ትን ትጠ​ብ​ቃ​ትና ትቀ​ድ​ሳት ዘንድ አዘ​ዘህ።