የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




ዘዳግም 24:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“አዲስ ሚስ​ትም ያገባ ሰው ወደ ጦር​ነት አይ​ሂድ፤ ምንም ነገር አይ​ጫ​ኑ​በት፤ ነገር ግን አንድ ዓመት በቤቱ በፈ​ቃዱ ይቀ​መጥ፤ የወ​ሰ​ዳ​ት​ንም ሚስ​ቱን ደስ ያሰ​ኛት።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አዲስ ሚስት በቅርብ ጊዜ ያገባ ሰው፣ ለጦርነት አይሂድ፤ ወይም ሌላ ሥራ እንዲሠራ አይገደድ። ለአንድ ዓመት ነጻ ሆኖ ቤቱ ይቈይ፤ ያገባትን ሚስቱን ደስ ያሰኛት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“አዲስ ሚስት በቅርብ ጊዜ ያገባ ሰው፥ ለጦርነት አይሂድ፤ ወይም ሌላ ሥራ እንዲሠራ አይገደድ። ለአንድ ዓመት ነጻ ሆኖ እቤቱ ይቆይ፤ ያገባትን ሚስቱን ደስ ያሰኛት።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“አዲስ ሚስት ያገባ ሰው ወታደር ሆኖ ለማገልገል አይገደድ፤ ሌላም ተጽዕኖ አይደረግበት፤ ለአንድ ዓመት ከማናቸውም ግዴታ ነጻ ሆኖ በቤቱ ሚስቱን ደስ ያሰኛት።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አዲስ ሚስትም ያገባ ሰው ወደ ጦርነት አይሂድ፥ ነገርም አይጫኑበት፤ ነገር ግን አንድ ዓመት በቤቱ በፈቃዱ ይቀመጥ፥ የወሰዳትንም ሚስቱን ደስ ያሰኛት።

ምዕራፉን ተመልከት



ዘዳግም 24:5
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ​ዚህ ሰው አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ይተ​ዋል፤ ሚስ​ቱ​ንም ይከ​ተ​ላል ፤ ሁለ​ቱም አንድ ሥጋ ይሆ​ናሉ።


የውኃ ምንጭህ ለአንተ ይሁንልህ፤ ከልጅነት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ።


በሕ​ይ​ወ​ትህ፥ አን​ተም ከፀ​ሓይ በታች በም​ት​ደ​ክ​ም​በት ድካም ይህ ዕድል ፈን​ታህ ነውና ከንቱ በሆነ በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ፥ ከፀ​ሓይ በታች በሰ​ጠህ፥ በከ​ንቱ ዘመ​ንህ ሁሉ፥ ከም​ት​ወ​ድ​ዳት ሚስ​ትህ ጋር ደስ ይበ​ልህ።


ሦስ​ተ​ኛ​ውም፦ ሚስት አግ​ብ​ች​አ​ለሁ፤ ስለ​ዚህ ልመጣ አል​ች​ልም በለው አለው።


ነገር ግን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን እን​ዲህ ይቀ​ናል፤ የዚህ ዓለም ኑሮ ሁሉ ሊያ​ልፍ ቀር​ቦ​አ​ልና፤ አሁ​ንም ያገቡ እን​ዳ​ላ​ገቡ ይሆ​ናሉ።


ሚስ​ትም አጭቶ ያላ​ገ​ባት ሰው ቢኖር በጦ​ር​ነት እን​ዳ​ይ​ሞት ሌላም ሰው እን​ዳ​ያ​ገ​ባት ወደ ቤቱ ተመ​ልሶ ይሂድ።


“የሰ​ውን ነፍስ እንደ መው​ሰድ ነውና ወፍጮ ወይም መጅ ስለ መያዣ ማንም አይ​ው​ሰድ።