ዳዊትም ከእርሱ ሺህ ሰረገላዎችን፥ ሰባት ሺህ ፈረሰኞችን፥ ሃያ ሺህም እግረኞችን ያዘ፤ ዳዊትም የሰረገለኛውን ፈረስ ሁሉ ቋንጃ ቈረጠ፤ ለራሱም መቶ ሰረገላዎችን ብቻ አስቀረ።
ዘዳግም 17:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእርሱ ፈረሶችን እንዳያበዛ፥ ሕዝቡንም ወደ ግብፅ እንዳይመልስ፤ እግዚአብሔር፦ በዚያች መንገድ መመለስን አትድገም ብሎአልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም ብዙ ፈረሶችን ለራሱ አያብዛ፤ ወይም ደግሞ የፈረሰኞችን ቍጥር ለመጨመር ሕዝቡን ወደ ግብጽ አይመልስ፤ እግዚአብሔር፣ “በዚያ መንገድ ፈጽሞ አትመለሱ” ብሏችኋልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንጉሡም ብዙ ፈረሶችን ለራሱ አያብዛ፤ ወይም ደግሞ ፈረሰኞች ለማብዛት ሕዝቡን ወደ ግብጽ አይመልስ፤ ጌታ፥ ‘በዚያ መንገድ ፈጽሞ አትመለሱ’ ብሎአችኋልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያም ንጉሥ ለሠራዊቱ ብዙ ፈረሶች ያሉት መሆን የለበትም፤ እግዚአብሔር ሕዝቡ ወደ ግብጽ እንዳይመለሱ ስለ አዘዘ ፈረሶችን ለመግዛት ወደ እዚያ ሰዎችን አይላክ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ለእርሱ ፈረሶችን አያበዛም፤ እግዚአብሔር፦ በዚያ መንገድ ደግማችሁ አትመለሱም ብሎአችኋልና ፈረሶችን ለማብዛት ሕዝቡን ወደ ግብፅ አይመልስም። |
ዳዊትም ከእርሱ ሺህ ሰረገላዎችን፥ ሰባት ሺህ ፈረሰኞችን፥ ሃያ ሺህም እግረኞችን ያዘ፤ ዳዊትም የሰረገለኛውን ፈረስ ሁሉ ቋንጃ ቈረጠ፤ ለራሱም መቶ ሰረገላዎችን ብቻ አስቀረ።
የአጊትም ልጅ አዶንያስ፥ “ንጉሥ እሆናለሁ” ብሎ ተነሣ፤ ሰረገሎችንና ፈረሰኞችን በፊቱም የሚሮጡ አምሳ ሰዎችን አዘጋጀ።
አሁንም ከወገኔ እንደ ሲዶናውያን እንጨት መቍረጥ የሚያውቅ እንደሌለ ታውቃለህና የዝግባ ዛፍ ከሊባኖስ ይቈርጡልኝ ዘንድ አገልጋዮችህን እዘዝ፤ አገልጋዮቼም ከአገልጋዮችህ ጋር ይሁኑ፤ የአገልጋዮችህንም ዋጋ እንደ ተናገርኸው ሁሉ እሰጥሃለሁ።”
የሰሎሞን ፈረሶች መምጫ ከግብፅና ከቴቁሄ ምድር ነበር። በዋጋ ገዝተው ከቴቁሄ የሚያመጡአቸውም ከሀገር ሽማግሌዎች የሆኑ የሰሎሞን ነጋዴዎች ነበሩ።
ሰሎሞንም ለሰረገሎች አራት ሺህ እንስት ፈረሶችና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሰኞች ነበሩት፤ በሰረገሎችም ከተሞች፥ ከንጉሡ ጋር በኢየሩሳሌም አኖራቸው።
እንዲህም ሆነ፤ ፈርዖን ሕዝቡን በለቀቀ ጊዜ፥ ምንም ቅርብ ቢሆን እግዚአብሔር በፍልስጥኤማውያን ምድር መንገድ አልመራቸውም፤ እግዚአብሔር፥ “ሕዝቡ ሰልፉን በአየ ጊዜ እንዳይጸጽተው፥ ወደ ግብፅም እንዳይመለስ” ብሎአልና።
ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡን በዙሪያ መንገድ በኤርትራ ባሕር ባለችው ምድረ በዳ መራቸው። የእስራኤልም ልጆች በአምስተኛው ትውልድ ከግብፅ ምድር ወጡ።
ሙሴም ለሕዝቡ፥ “አትፍሩ፤ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘለዓለም አታዩአቸውምና ቁሙ፤ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ።
ምድራቸውም በብርና በወርቅ ተሞልታለች፤ ለመዛግብቶቻቸውም ቍጥር የለውም፤ ምድራቸውም ደግሞ በፈረሶች ተሞልታለች፤ ለሰረገሎቻቸውም ቍጥር የለውም።
እናንተ የይሁዳ ቅሬታ ሆይ! እግዚአብሔር፦ ወደ ግብፅ አትግቡ ብሎ ተናግሮባችኋልና ዛሬ እንዳስጠነቀቅኋችሁ በእርግጥ ዕወቁ።
እርሱ ግን በእርሱ ላይ ሸፈተ፤ ፈረሶችንና ብዙንም ሕዝብ ይሰጡት ዘንድ መልእክተኞችን ወደ ግብፅ ላከ። በውኑ ይከናወንለት ይሆን? ይህንስ ያደረገ ያመልጣልን? ቃል ኪዳንንስ ያፈረሰ ያመልጣልን?
ከእናንተ ጋር ቃልን ውሰዱ፤ ወደ እግዚአብሔርም ተመለሱ። እንዲህም በሉት፥ “ኀጢአትን ሁሉ አስወግድ፤ በቸርነትም ተቀበለን፤ በወይፈንም ፈንታ የከንፈራችንን ፍሬ ለአንተ እንሰጣለን።
ከእንግዲህ ወዲህ ተመልሰህ አታያትም ባልሁህ መንገድም እግዚአብሔር በመርከብ ወደ ግብፅ ይመልስሃል፤ በዚያም ለጠላቶቻችሁ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮች ትሆናላችሁ፤ የሚራራላችሁም አይኖርም።”
እንዲህም አለ፥ “በእናንተ ላይ የሚነግሠው የንጉሡ ሥርዐት ይህ ነው፤ ወንዶች ልጆቻችሁን ወስዶ ሰረገላ ነጂዎችና ፈረሰኞች ያደርጋቸዋል፤ በሰረገሎችም ፊት ይሮጣሉ፤